የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ: post #2483 — TG.ME

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባPhoto
“በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!”
በአዲስ አበባ ከተማ የ2018 ዓ.ም ዐበይት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞችና ዝርዝር መርሀ ግብሮች፤
1) ሰብዓዊና ማህበራዊ አገልግሎት፤
· ቤት ግንባታ መርሀ-ግብር፡- 2500 ቤቶችን በመገንባት ለ12,500 አረጋውያን ፣ አቅመ ደካሞች ፣ አካል ጉዳተኞችን ፣ የሀገር ባለውለታዎች እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይደረጋሉ፤ በቤት ግንባታ ስራ 7,500 በጎ ፈቃደኞችን ይሳተፋሉ፤
· ማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር፡ 8,150 በጎ ፈቃደኞችን ማሳተፍ፤ 205,000 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
· የትስስር መርሀ ግብር፡- በአንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው የትስስር መርሃ ግብር 33,000 የህብረተሰብ ክፍሎችን ቢያንስ ለ3 ወራትና ከዚያ በላይ የሚዘልቅ ትስስር ይፈጠራል፤ 220 ወላጆቻቸውን ያጡና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት አማራጭ ድጋፍ  ይመቻችላቸዋል፡፡
2) ልዩ ፍላጎት አገልግሎት፤
· ለ12 የአምዕሮ ህሙማን፣ የአረጋዊያንና የህፃናት መርጃ ማዕከላት በመጎብኘ  የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ 4800 ወገኖች ተጠቃሚ ይሆናሉ፤
· በ11 ልዩ ፍላጎት የሚሹ ወገኖች ክብካቤ ማዕከላት፣ ተቋማት/ማህበራት  1,100 በጎ ፈቃደኞችን በማሳማራት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡
3)አረንጓዴ አሻራና አካባቢ ጥበቃ አገልግሎት፤
· በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር፡- 400,000 የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተሳታፊ ማድረግ፡፡
· በአካባቢ ጽዳት፣ ማስዋብና እንክብካቤ መርሀ ግብር፡- 100,000 የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ፡፡
4) ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት፤
· በህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና በኮሪደር ልማት ጥበቃና ማስተባበር መርሀ-ግብር፡-  1,100 በጎ ፈቃደኞችን ይሳተፋሉ፡፡
5) ትምህርት እና ስልጠና አገልግሎት፤
· በክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት መርሀ ግብር፡- በ5 ዋና ዋና የትምህርት ዓይነቶች 41,800 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
· በአጫጭር የክህሎት ስልጠና መርሀ ግብር፡- በመሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠናና በአጫጭር የክህሎት ስልጠናዎች ላይ 6,600 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል፡    
· በጎልማሶች ትምህርት መርሀ ግብር፡- 5,500 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል፡፡
6) የጤና አገልግሎት፤
· በነፃ ህክምና አገልግሎት  መርሀ ግብር፡- የመንግስትና የግል የህክምና ተቋማትንና የህክምና ቡድኖችን በማሳተፍ ለ110,000 የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ይሰጣል፡፡
· በጤና መድህን ደጋፍ መርሃ ግብር፡- ለ 5500 ያህል አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ዓመታዊ የጤና መድህን ሽፋን ድጋፍ ያገኛሉ፤
· በደም ልገሳ መርሀ ግብር፡- 25,000 ዩኒት ደም ይሰበሰባል፤
· በበጎነት በሆስፒታልና በጤና ጣቢያ መርሀ ግብር፡- 3,300 በጎ ፈቃደኞች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ይሰማራሉ፤ በ12 የመንግስት ሆስፒታሎች ለ1200 ህሙማን የተለያዩ ድጋፎች ይደረጋሉ፡፡
· የመድኃኒት ድጋፍ መርሃ ግብር፡- በህመም ላይ ሆነው የገንዘብ አቅም ለሌላቸው 2,200 የህበረተሰብ ክፍሎች ከግል ፋርማሲዎች ጋር ትስስር በመፍጠር የመድኃኒት ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
7) የስፖርት ንቅናቄ አገልግሎት፤
· 1,100 በጎ ፈቃደኛ የስፖርት ባለሙያዎችን በማሳተፍ የተለያዩ ስፖርታዊ ስልጠናዎችን እንዲሰጡ ይደረጋል፤
8)የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አገልግሎት፤
· በተመረጡ አደባባዮች ላይ 10,000 በጎ ፈቃደኞን በማሰማራት የትራፊክ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡
9)በተቋማት የበጎ ፈቃድ ድጋፍ አገልግሎት፤ 
· ተገልጋይ በሚበዛባቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት 10,000 በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
10)የሙያ በጎ ፈቃድ አገልግሎት፤
· 22,000 በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች በሙያቸው አገልግሎት እንዲሰጡ ይይረጋል፤ (መምህራን፤ ሃኪሞች፣ ሌሎች)
11)የትውልድ ግንባታ አገልግሎት፤
· በህይወት ልምድ ማካፈል መርሀ ግብር፡- 1,100 ወጣት በጎ ፈቃደኞች ፤ በተለያየ ዘርፍ ስኬትን ካስመዘገቡ ታላላቅ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች፣ ከስኬታማ ወጣቶች የህይወት ልምድና ተሞክሮ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡
· በቤተ መፅሐፍት ድጋፍ መርሀ ግብር፡- በጎ ፈቃደኞችንና ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ 5,500 መጻህፍትን ለማሰባሰብና ለ11 የትምህርት ቤት መፅሐፍት ቤቶች ድጋፍ ለማድረግ ታቅዷል፡፡
12)   የሰላም እሴት ግንባታ አገልግሎት፤
· በሐይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ላይ 50,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ እንዲያሰተባብሩና የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎችን እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡
13) ማኅበራዊ ሚዲያ ለበጎነት አገልግሎት፤
· ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ ተግባር እንዲውል 12,000 ወጣቶችን ስልጠናና ግንዛቤ በመፍጠር በማህበራዊ ሚድያው በጎ ተፅኖ እንዲፈጥሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
14)   የአደጋ ቅድመ - መከላከል አገልግሎት፤
· ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት የሚሰሩ 2,200 ቅድመ ስልጠና የወሰዱ የአደጋ ተከላካይ በጎ ፈቃደኞች ይሰማራሉ፤
· 110 በጎ ፍቃደኞች በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ወቅት የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ ስልጠና ይወስዳሉ፡፡
15)   የከተማ ግብርና ልማት አገልግሎት፤
· 11,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ በህዝብ ተቋማትና በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን ወደ ምርታማ የጓሮ አትክት ስፍራ የመለወጥ ስራ ይከናወናል፡፡
· 550 በግብርና ሙያ የተመረቁ ተማሪዎችና ባለሙያዎች በከተማ ግብርና ሳይንስ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲሰጡ ይደረጋል፤፤
16)ወሰንና ድንበር የለሽ አገልግሎት፤
·  በወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር፡- 1,500 በጎ ፈቃደኞችን በተመረጡ ክልሎች በማሰማራት የከተማችንን የበጎ ፈቃድ ተሞክሮ የማስፋፋት ስራ ይከናወናል፡፡
· በስጦታዬ ለሀገሬ መርሀ ግብር፡- የተለያዩ የትምህርት መሳሪያዎችን፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችንና አልባሳትን በማሰባሰብ ለ5,200 የክልል እና አጎራባች አካባቢ ተማሪዎችማ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ይደረጋል፡፡
· በድንበር የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር፡- 30 በጎ ፍቃደኞችን በአጎራባች ሃገራት በአረንጓዴ አሻራ  ተግባር ላይ በማሳተፍ በቀጠናው ያለውን ወንድማማችነትና የህዝብ ለህዝብ ትስስር  የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡
“በጎነት፤ ለአዲስ አበባ ከፍታ!”
June 22, 2026 388 1