Anthropic ለ-Claude የ-AI ኤጀንቶች 16 ባዮሎጂካል ኢላማዎችን (Biological targets) የሰጠ ሲሆን ኤጀንቱ 1,320 አዳዲስ ፕሮቲኖችን ዲዛይን አድርጎ 354ቱ በቤተ ሙከራ በተደረገ ፍተሻ በትክክል መስራታቸው ተረጋግጧል። በተሞከሩት 15 ኢላማዎች ውስጥ ለ14ቱ ውጤታማ ባይንደሮችን ያመነጨ ሲሆን ያስመዘገበው ከ22.6% እስከ 35.1% የስኬት መጠን (Hit rate) ከተለመደው የ10–15% የዲዛይን አሰራር በ2 እስከ 3 እጥፍ ብልጫ ያለው ነው።
ይህ ውጤት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለህክምና እና ለመድኃኒት ቅመማ የሚሆኑ አዳዲስ ባዮሎጂካል ሞለኪውሎችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ፍጥነትና ትክክለኛነት ዲዛይን ለማድረግ ያለውን የላቀ አቅም ያሳያል።
@AddisIntel