"የአንድ መንደር ነዎሪዎች ተጠርገው ሄደዋል!" - ከአደጋው የተረፈ‼️
* በኔፓል የደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 160 የደረሰ ሲሆን የበርካታ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ደህንነት አሁንም አሳሳቢ ሆኗል።
በሰሜናዊ ኔፓል ራሱዋ በተባለው የተራራማ አካባቢ እ ኤ አ ኦገስት 26 ቀን 2026 በድንገት በተከሰተ የበረዶ እና የዓለት መደርመስ ምክንያት የተነሳው የጎርፍ አደጋ ከፍተኛ የሰው ሕይወት እና የንብረት ጉዳት አድርሷል።
የኔፓል ፖሊስ እና የቻይና ቲቤት ባለስልጣናት እስካሁን የ160 ሰዎችን አስከሬን ማግኘታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በርካታ አስከሬኖች በጭቃ እና በፍርስራሾች ውስጥ ተቀብረው በመገኘታቸው የሟቾች ቁጥር የበለጠ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጧል።
የኔፓል ቱሪዝም ቦርድ እንደተናገረው በአደጋው ቀጠና 105 የህንድ፣ 54 የአሜሪካ፣ 34 የአውስትራሊያ፣ 33 የእንግሊዝ፣ 24 የካናዳ፣ 19 የማሌዢያ እንዲሁም የሌሎች ሀገራት ዜጎችን ጨምሮ በድምሩ 384 ጎብኚዎች የት እንደገቡ ማወቅ አልተቻለም።
አደጋው በማለዳ ወቅት የተከሰተ በመሆኑ እና የቱሪስት ማረፊያዎች እንዲሁም የኮሚዩኒኬሽን መስመሮች ሙሉ በሙሉ በመውደማቸው ከተጓዦቹ ጋር ግንኙነት ማድረግ አልተቻለም።
ይህንን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት መንግስታት ከፍተኛ ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
የኔፓል መንግስት አካባቢውን የአደጋ ጊዜ ቀውስ ቀጠና ብሎ ያወጀ ሲሆን የህንድ፣ የአሜሪካ እና የእንግሊዝ መንግስታት ከኔፓል የነፍስ አድን ቡድኖች ጋር በመተባበር የጠፉ ዜጎቻቸውን ለመፈለግ እየሰሩ ነው።
ከእንደዚህ አይነት ድንገተኛ አደጋ ይሰውረን።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14
13
2August 27, 2026 3.5K 6