አደጋው ያጋጠመው የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ቋንቋ ት/ት ክፍል ህንጻ ላይ ነው " ዛሬ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ… — AAU GENERAL — TG.ME

" አደጋው ያጋጠመው የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ቋንቋ ት/ት ክፍል ህንጻ ላይ ነው "

ዛሬ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ውስጥ በሚገኘው የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ቋንቋ ት/ት ክፍል ህንጻ ላይ እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

አደጋው በዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና በፀጥታ ሀይሎች እና የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች ብርታት በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ ከወላይታ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በአደጋው የደረሰው ጉዳት እና መንስኤ እየተጣራ ይገኛል።
❤2
September 3, 2026 647 1