Universty Placement ‼️ የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና… — AAU GENERAL — TG.ME

Universty Placement ‼️

የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
 
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን ከነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ምርጫችሁን ት/ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ እራሳችሁ በመሙላት እንድታሳውቁ እንገልጻለን።

ማስፈንጠሪያ (Link)  https://student.ethernet.edu.et/

ማሳሰቢያ፡- የህክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከ6 ወር በታች ህፃን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል።

@AAU_GENERAL
❤2
September 3, 2026 713 36