FYI በነሐሴ 2018 ዓ.ም የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዱ የጤና ባለሙያዎች ውጤት ተለቋል፡፡ በነሐሴ 2018… — AAU GENERAL — TG.ME

#FYI

በነሐሴ 2018 ዓ.ም የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዱ የጤና ባለሙያዎች ውጤት ተለቋል፡፡


በነሐሴ 2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር የተሰጠውን የጤና ሙያ የብቃት መዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባትና የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከዛሬ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁ. 952 በሥራ ሰዓት በመደወል ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በማሳወቅ ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

በዚህ ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ ተመዛኞች በተናጠል የውጤት ትንተና (Domain Analysis) ማየት እንደምትችሉ የተገለፀ ሲሆን፣ ይህም ራችሁን ለማሻሻልና የበለጠ ለማብቃት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከሰኞ ዻጉሜን 02/2018 ዓ.ም  ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል የሚላክ ስለሆነ የሙያ ፍቃዳችሁን 12ኛ ክፍል በተማራችሁበት ክልል ማውጣት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቱሩ አሳውቋል፡፡

#tikvahuniversity

@AAU_GENERAL
September 2, 2026 566