ከአደጋ የዳነው የ10 ሴኮንድ እድለኛ
የደህንነት ካሜራ ምስል በአስገራሚ ሁኔታ ህይወቱ ከተሰወረ አደጋ የተረፈን ሰው ታሪክ ይፋ አድርጓል።
ግለሰቡ ግቢውን አቋርጦ ወደ መኖሪያ ቤቱ በሰላም ሲገባ ምንም አይነት የስጋት ምልክት አልነበረም።
ነገር ግን ቤቱ ውስጥ በገባ በ10 ሴኮንዶች ውስጥ፡ እሱ ያልፈበት መንገድ ላይ አንድ ትልቅ ዛፍ ተደርምሶ ወደቀ።
በስፍራው ጥቂት ሴኮንዶች ዘግይቶ ቢሆን ኖሮ ሊደርስበት የሚችለው ጉዳት የከፋ ይሆን ነበር።
ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትልቅ ትኩረት ያገኘ ሲሆን፡ ብዙዎች ግለሰቡ ሁለተኛ ልደቱን ማክበር እንዳለበት አስተያየት ሰጥተዋል።
ይህ አጋጣሚ በጥቂት ሴኮንዶች ልዩነት ውስጥ በህይወትና በሞት መካከል ያለው መስመር ምን ያህል ቀጭን እንደሆነ ሌላ ማረጋገጫ ሆኗል።
@AAU_GENERAL
6September 2, 2026 745 2