ቀን 14/12/2018 ዓ ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዛሬዉ ቀን ለግብር ከፋዮች በኢ-ፋይሊንግ እና በኢ ፔይመንት ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በኢ-ፋይሊንግላይ ስልጠናዉን የሰጡት የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ግብይት ድጋፍና ክትትል የስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰይድ መሐመድ ሲሆኑ በዚሁ ወቅት ግብር ከፋዩ ይህንን ቴክኖሎጂ በአግባቡ በመጠቀም በተለይ በVAT Sales Details and Uploading ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝቧል፡፡ በዚሁ መድረክ ላይም በኦንላይን ያሳወቁ ግብር ከፋዮች በኦንላይን ክፍያ መፈጸም እንዳለባቸዉ የኢ ፔይመንት ቡድን አስተባባሪ የሆኑት አቶ እንድሪስ መሐመድ በሰፊዉ አብራርተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃን ደምሴ በመድረኩ ላይ በመገኘት በስልጠናዉ ርዕስ ላይ እና በሌሎች የታክስ ህጎችና ተያያዥ ወቅታዊ ግብር ከፋዩ ሊተገብራቸዉ የሚገቡት ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
በመድረኩም ከሰልጣኞች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ምላሽም ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ስልጠናዉ አስፈላጊ እና ወቅቱን የጠበቀ በመሆኑ ለስራቸዉ በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ሰልጣኞቹ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡
የላቀ ገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልጽግና!


















