"ሰላም ዶክተር ልጄ የ1 ዓመቱ ነው። ፎቶ ላይ እንደሚታየው በአንገቱ ፊት ለፊት ላይ እብጠት አለው። ይህ ምን ሊሆን ይችላል? ስለዚህ ጉዳይ በደንብ ብታብራራልኝ!"
(የወላጅ ጥያቄ)
🌡ውድ ጠያቂያችን ስለ ጥያቄው በጣም እናመሰግናለን!
🌡ይህ ችግር በጣም የተለመደ እና በየቀኑ ከምናያቸው ችግሮች መካከል አንዱ ነው! ይህም ችግር Thyroglossal Duct Cyst ይባላል!
🌡በልጆች በአንገት ላይ የላይኛው ወይም መካከለኛው የፊት ክፍል ላይ ህመም የማያሳይ እብጠት ሲሆን አንዳንዴም ፈሳሽ ሊፈነዳ እና ፊስቱላ ሊፈጥር የሚችል ችግር ነው።
🌡ከአፈጣጠር ጋር የተያያዘ ችግር ሲሆን የካንሰርነት ባህሪ የሌለው እብጠት ነው።
✍ጥያቄ-1፡ Thyroglossal Duct cyst ምንድን ነው?
🌡አንድ ጽንስ እያደገ ሲሄድ የታይሮይድ ዕጢ ከምላስ አካባቢ በመነሳት የታችኛው የአንገት ክፍል መውረድ አለበት።
🌡የሚወርድበት መንገድ ብዙውን ጊዜ ምንም ዱካ አይተውም። መዘጋት አለበት!
🌡 የዚህ መንገድ ትንሽ ክፍል ከቀረ በፈሳሽ ሊሞላና የታይሮግሎሳል ቱቦ ሲስት (Thyroglossal Duct Cyst) ሊፈጥር ይችላል።
✍ጥያቄ-2፡- ለምን አሁን ታዬ? ለምን እንደ ተወለደ አልታየም?
🌡ክፍተተቱ ልጆች ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ይኖራል። ከላይ በአይናችን ላናየው እንችላለን!
🌡ነገር ግን ከጊዜ በኋላ ብዙውን ጊዜ ከ1-5 ዓመት አካባቢ ፣ በተለይም ከጉንፋን ወይም ከጉሮሮ ኢንፌክሽን በኋላ ሊታወቅ ይችላል፣ ይህም እብጠቱን ሊያባብሰው ይችላል።
✍ጥያቄ -3 ፡- አደገኛ ነው? ካንሰርነት ባህሪ ይኖረው ይሆን?
🌡ያን ያክል አደገኛ የሚባል ችግር አይደለም።
🌡በልጆች ላይ ይህ ሁኔታ ሁልጊዜ ማለት ይቻላል የካንሰርነት ባህሪ ያለው አይደለም።
🌡ለወደፊቱ ከእዚህ እብጠት የሚነሳ ካንሰር እጅግ በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ሲሆን ብዙውን ጊዜ በአዋቂዎች ላይ እንጂ በትናንሽ ልጆች ላይ አይታይም።
✍ጥያቄ-4 ፡- ይህ እብጠት መኖር አለመኖሩን እንዴት ይታወቃል?
🌡 በአካል ምርመራ በምናደርግበት ጊዜ እንደሚከተለው ሆኖ ሊታይ ይችላል!
💊💊በአንገታቸው መሃል ላይ ለስላሳ፣ ክብ እብጠት
💊💊 ሲውጡ ወይም ምላሳቸውን ወደ ውጭ ሲያወጡ ወደ ላይ እና ወደ ታች ሲንቀሳቀስ ይታያል!
🌡🌡ብዙውን ጊዜ ኢንፌክሽን ካልፈጠረ ስቃይ እና ህመም የለውም
✍ጥያቄ -5 ፡ የልጄን መተንፈስ፣ አመጋገብ ወይም ንግግር ላይ ተጽዕኖ ያደርስበት ይሆን?
🌡አብዛኛውን ጊዜ ይህን አይነት ችግር አያስከትልም።
🌡እነዚህ ችግሮች የሚከሰቱት ሲስቱ ከተበከለ( if it is superinfected) ወይም በጣም ትልቅ ከሆነ ብቻ ነው።
✍ጥያቄ-6፥ ተጨማሪ ምርመራዎች ያስፈልጉት ይሆን?
🌡አብዛኛውን ጊዜ የአንገት አልትራሳውንድ ምርመራ በቂ ነው።
🌡 የብጠት መኖሩን እና ከሌሎች እብጠት ምክንያቶች መለየት ይቻላል!
🌡ሌላው የታይሮይድ ዕጢ በተለመደው ቦታ ላይ መሆኑን ያረጋግጣል።
🌡 የደም ምርመራ እምብዛም አያስፈልግም።
✍ጥያቄ -7፡- ህክምና ያስፈልገዋል?
🌡አዎ!
🌡 የመጨረሻው ሕክምና ቀዶ ጥገና ነው!
🌡 ቀዶ ጥገናው Sistrunk Procedure ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም እብጠቱን ከስሩ እና አብሮ የተያያዘውን መካከለኛ የhyoid አጥንት ክፍል የማስወገድ ሂደት ነው!
🌡ይህም እንደገና እንዳይከሰት ይከላከላል።
🌡ቀዶ ጥገናው ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው ህፃኑ ጤናማ እና ምንም አይነት ኢንፌክሽን በሌለበት ጊዜ መሆን ይኖርበታል ።
✍ጥያቄ - 8፡ ባይታከም ምን ሊያስከትል ይችላል?
🌡ካልታከመ የሚከተሉትን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል፡
🩺በተደጋጋሚ ኢንፌክሽን መፍጠር
🩺ሊፈነዳ ወይም ፊስቱላ ሊፈጥር ይችላል!
🩺ከጊዜ በኃላ ከዚህ እብጠት ካንሰር ሊነሳ ይችላል!
🌡ስለዚህ እብጠቱ ህመም የሌለው ቢሆንም እንኳ በቀዶ ጥገና ማስወገድ ይመከራል።
✍ጥያቄ - 9፡- ቀዶ ጥገናው ለአንድ ዓመት ልጅ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?
🌡 አዎ!
🌡ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ከተሰራ በጣም የተለመደ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የህፃናት ቀዶ ጥገና አይነት ነው።
🌡ልጆች ከዚህ ህክምና በኋላ በፍጥነት በማገገም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ።
✍ጥያቄ- 10 ፡- ከቀዶ ጥገና በኋላ ተመልሶ ይመጣል ወይ?
🌡ቀዶ ጥገናው በትክክል ከተደረገ በድጋሚ የመምጣት እድሉ በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ነው።
💊በመጨረሻም ውድ ጠያቂያችን ይህ ችግር በልጆች ላይ የተለመደና ሊታከም የሚችል ችግር ሲሆን በተገቢው ህክምና መስተካክል የሚችል እንደሆን መረዳት ያስፈልጋል።
❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለሌሎችም ወላጆች እንዲደርስ በቅንነት #share ያድርጉት ‼️🙏
📘በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ ጥያቄ መጠየቅ ከፈለጉ ወይም በሌሎች ጉዳዬች በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል።
👇👇👇👇👇👇
📲+251911441651
🌡🙏ሌሎች መረጃዎች ሲለቀቁ እንዲደርሷችሁ የtelegram አድራሻችንን ይቀላቀሉ!
http://t.me/DrSaleamlakT
ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!
አዘጋጅ :-
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር (YK12HMC)
Dr. Saleamlak Tigabie: MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at YK12HMC) ,Addis Ababa, Ethiopia
Telegram
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና ረ. ፕሮፌሰር (Ass. Prof. Of Pediatric Surgery)
@ ከ18 አመት በታች ለሆኑ ህፃናትና ታዳጊዎች(0911441651)@Addis Ababa
✅️የኩላሊት እና የሽንት ቱቦ ቀዶ ህክምና
✅️የብልት አፈጣጠር ችግር
✅️የዘር ፍሬ አቀማመጥ ችግር
✅️የግርዛት አገልግሎት
✅️ጠቅላላ የአንጀት ቀዶ ህክምና
✅️የሰገራ መውጫ አፈጣጠር ችግር ሕክምና
✅️ማንኛውንም የህፃናት ቀዶ ህክምና አገልግሎትን እንሰጣለን

9
1
1March 3, 2026 2.3K 1