ይህ ታሪክ የሚጀምረው ከአመታት በፊት በአዲስ አበባ በ Mother Teresa's Missionaries of Charity ውስጥ ነው።
መስፍን በወቅቱ በልብ ህመም ምክንያት ለሞት ተቃርቦ የነበረ ምስኪን ታዳጊ ነበር። ሆኖም ግን፣ በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትን ህይወት የታደገውና ደግነቱ በዓለም የታወቀው አሜሪካዊው ዶክተር ሪክ ሆድስ (Dr. Rick Hodes) መስፍን ላይ ተስፋ አልቆረጠም ነበር። ሪክ መስፍን ወደ አሜሪካ አትላንታ ሄዶ የቀዶ ጥገና ህክምና እንዲያገኝ በማድረግ ህይወቱን ከሞት አፋፍ መለሰው።
ነገሩ የሚገርመው እዚህ ጋር ነው! መስፍን ከህክምናው በኋላ በሪክ ሆድስ ድጋፍና ምክር ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ፤ ዛሬ እሱም እንደ ሪክ ሆድስ ጎበዝ የቀዶ ጥገና ሀኪም ለመሆን በቅቷል። አሁን በያዝነው Jan 2026፣ መስፍን እና ህይወቱን የታደገው ዶክተር ሪክ ሆድስ በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድነት ሆነው ለምስኪን ህፃናት ቀዶ ጥገና እያደረጉ ይገኛሉ።
መስፍን በአንድ ወቅት ራሱ በታካሚነት የተረገጠበትን የቀዶ ጥገና ክፍል፤ ዛሬ ደግሞ እንደ ሪክ ሆድስ የሌሎችን ህይወት ለመታደግ ሰርጅን ሆኖ ሲገባ ማየት እጅግ አስደናቂ ነው! የዚህ ወጣት ታሪክ ውለታን መመለስ እና ለሰው ልጆች መድረስ ምን ያህል ታላቅነት እንደሆነ ያስተምረናል።
ለካስ ደግነት እንደ ዘር ነው፤ ዛሬ የተከልከው ነገር ነገ ፍሬ ሆኖ አንተን ራሱ ይረዳሃል! ሪክ ሆድስ መስፍንን አዳነ፤ ዛሬ መስፍን ደግሞ ሪክ ሆድስን እያገዘ ሌሎችን እያዳነ ነው።
ለሰው ልጅ ደግነት ይኑረን!

24
3
2
2February 1, 2026 3.8K 2