#conservative_Vs_liberal ክርስትያን
በአንድ ጉዳይ ላይ conservative ወይም liberal ነኝ ከማለታችን በፊት ስለ ጉዳዩ ተመጣጣኝ እውቀት መያዝ ይቀድም ነበር።
ይሁንና፦
በአንድ በኩል ለሃይማኖቴ ወግ አጥባቅም ጠባቂም ነኝ ይልህና ስለ ሥነ ፍጥረትም ሆነ ስለ ነጻ ፈቃድ ምንም ተምሮ ወይም አንብቦ ሳይረዳ በአንድ ባለ ዊግ ተገርፎ "ቡና የተረገመ ተክል ስለሆነ የቡና ቁርስም የእርግማን መስዋዕት ነው" ብሎ "ወይ ፍንክች ያባ ብላዎ ልጅ" ይላል። በምጸአተ ክርስቶስ ካልሆነ በሌላ ላያምን ድርቅ።
በሌላ በኩል liberal የሚለውን ቃል ከቃላዊ ብያኔ ሳይዘል በአንድ ነጭ ሌክቸር ተደርጎ ስለ መሠረታዊ ነገረ ሃይማኖት በትንሹ ለማወቅም ለመጠየቅም ሳይሞክር "እኛ ስለ ምናካብድ እንጂ በ 'ክርስርያኖች' መኻልኮ መሠረታዊ የአስተምህሮ ልዩነት የለም" ይላል። ቀጥሎም የእግዚአብሔር ነጻ ፈቃድ ስጦታን ገፍትሮ "ደግሞ እግዚአብሔር ጨካኝ አይደለም " ብሎ በ liberalism የኖቤል ሽልማት ይጠብቃል።
2017 ዓ. ም
2August 5, 2026 100 1