ለአመታት ከዚህ አካውንትና ከኔ ከታናሹ አንደበት ብዙ ነገርን ተምራችኋል!! 1 :- እስኪ ምን ያህል ሰው በኔ… — 𝐘𝐎-𝐌𝐈-𝐅 ትንሹ ዘ❷❶ ✝️ — TG.ME

ለአመታት ከዚህ አካውንትና ከኔ ከታናሹ አንደበት ብዙ ነገርን ተምራችኋል!! 1 :- እስኪ ምን ያህል ሰው በኔ ቪዲዮዎች ተቀይሯል ወደ ራሱ ተመልሷል ንስሐ ገብቷል እራሱን ለውጧል?እስኪ በኮመንት ሳትዋሹ ንገሩኝ!! 2 :- አሁን ዮሚ ምንም መንፈሳዊ እውቀት ቢኖረውም ሥጋ ለባሽ ሰው ነውና ከደከመና በኃጢአትና በደል ከወደቀ ስለዚህ እዚህ ላይ ድክመቱን አለማሳየቱና ፍጹም ከድክመቱ ተቃራኒ ሰዉን ወደ ንስሐና ቅዱስ ቁርባኑ የሚጠራ ቪዲዮ መስራቱ ስህተት ነው?? 3 :- ስህተት ካልሆነስ ማስመሰል ነው? 4 :- ብዙዎች ድክመቴን አይተው ወይ እኔ እራሴ ስነግራቸው አንተ ሲጀመር አስመሳይ ነህ ይሄን content አቁም ወይም ቀይር ማለታቸው ትክክል ነው?? 5 :- እናንተስ መድከሜን ስታውቁ እንደ እነሱ ልትፈርዱብኝ ነው ማለት ነው?? ምክንያቱም ከብዙ ሰው እነዚህን ቃላት እየሰማሁ ስለሆነ ብዙ ላስተምራችሁ ብችልም ከዚህ በኋላም ብዙ ብትማሩብኝም ነገር የማስመሰል አገልግሎት እየመሰለኝ መቀጠል ፈራሁ ስለዚህ የሆነ ነገር ከመወሰኔ በፊት የእናንተን ሀሳብ ማወቅ ስለፈለኩ ነው!!ስለዚህ በቅንነት ከታች አሳውቁኝ!!!🙏😞

May 16, 2026 1.4K 1 1