MoE የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለ1 ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ… — Gion Media — TG.ME

#MoE

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለ1 ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፎርቹን ጋዜጣ ነው።


#gion@yegion
November 17, 2025 758