ሐሙስ:- ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ∙ም በፋዌ (FAWE) እና ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ዓመታዊ ጉባኤ ላይ… — General Wingate Polytechnic college-Official channel — TG.ME

ሐሙስ:- ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ∙ም
 
በፋዌ (FAWE) እና ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የኮሌጁ አሰልጣኝና ሰልጣኝ እውቅና ተበረከተላቸው፡፡
 
ኮሌጃችን በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል (AICC) በተካሄደው የፋዌ (FAWE) እና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን 2ኛ ምዕራፍ የ2026 ዓመታዊ የሰልጣኞች ጉባኤ ላይ በዛሬው ዕለት ተሳትፏል።
 
የአፍሪካ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች ፎረም (FAWE) ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የሚተገብረው ይህ የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተተገበረባቸው ሁለት ተቋማት አንዱ ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 59 የኮሌጁ ሰልጣኞች የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ናቸው።
 
በጉባኤው ላይ "የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞችን የተቅጣሪነት እና የስራ ፈጠራ እድሎች ማጠናከር" (Strengthening Employability and Entrepreneurship Pathways for TVET Students) በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት የተካሄ ሲሆን በውይይቱ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ ከፋዌ፣ ከኢንዱስትሪው ዘርፍ እና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጡ አመራሮች ተሳትፈዋል።
 
 ውይይቱ ሰልጣኞችን ከገበያው ፍላጎት ጋር የሚጣጣም ክህሎት በማስጨበጥ፣ የኢንዱስትሪ ትስስርን በማስፋት እና ለግል ስራ ፈጠራ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ዙሪያ ያተኮረ ነበር።
 
ከዕለቱ መርሃ-ግብር ክንዋኔዎች መካከል አንዱ የእውቅና እና ሽልማት ስነ-ስርዓት ሲሆን በዚህም በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በላቀ ስራ ሰልጣኞችን በማብቃትና በመደገፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የኮሌጁ የፊዚኮ-ኬሚካል አሰልጣኝ ወ/ሮ ጸሐይ አህመድ የታብሌት ሽልማት ሲበረከትላቸው በተመሳሳይ ከተቋማችን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበቺው ሰልጣኝ ሀና ቢራራ የስማርት ፎን ማበረታቻ ተሰጥቷታል፡፡  
 
ፋዌ (FAWE) ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች በሚገኙ 6 ፖሊ ቴክኒኮች ላይ እየሰራ ያለ ድርጅት ነው፡፡  
 
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
❤15
August 27, 2026 2.9K 4