ሐሙስ:- ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ∙ም አንጸባራቂ ድል ለጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ!! አንጋፋውና በክህሎት ስልጠና ዘርፍ ግንባር ቀደም የሆነው ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም በከተማ አቀፍ ደረጃ የ2ኛ ደረጃን ድል ተቀዳጅቷል። ኮሌጁ ይህንን ትልቅ ስኬት ያረጋገጠው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሥር በሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች መካከል በተካሄደው ምዘና ነው። በቢሮው በተካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የግብ ተኮር (KPI) እና የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም ምዘና መሠረት ኮሌጃችን 94.26% ከፍተኛ ውጤት ማምጣት ችሏል። ይህ ምዘና የተቋማትን የመማር ማስተማር ጥራት፣ የአሰራር ቅልጥፍና፣ የተገልጋይ እርካታን እንዲሁም በተቋማዊ አቅም ግንባታ የተከናወኑ ዐበይት ተግባራትን በሚገባ የፈተሸ ሲሆን ኮሌጁ በሁሉም መለኪያዎች ልቆ መገኘት ችሏል። ኮሌጁ ባስመዘገበው በዚህ የላቀ አፈጻጸም የዕውቅናና ሽልማት የምስክር ወረቀት የተሰጠው ሲሆን ይህ ክብር የተቋሙ አመራሮች፣ አሰልጣኝና የአስተዳደር ሠራተኞች ዓመቱን ሙሉ ላሳዩት ያላሰለሰ ጥረት፣ ቁርጠኝነት እና ጠንካራ የቡድን መንፈስ የተሰጠ እውነተኛ ማሳያ ነው። ይህ አሸናፊነት ኮሌጁ ለጥራት ማረጋገጥ ስርዓት የሚሰጠውን ከፍተኛ ትኩረትና ተቋማዊ አሰራሩን ለማዘመን እያደረገ ያለውን ስኬታማ ጉዞ በጉልህ የሚያንፀባርቅ ነው። የኮሌጁ ማህበረሰብ በዚህ በተገኘው ስኬት በመኩራት በቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት ከዚህም የላቀ ደረጃ ለመድረስና የ1ኛ ደረጃ አሸናፊነትን ለመቀዳጀት በበለጠ ተነሳሽነት ዝግጅቱን ጀምሯል። ለዚህ ታላቅ ስኬት መገኘት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከታችሁ የኮሌጃችን ቤተሰቦች በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችንን እያስተላለፍን በቀጣይ የጀመርነውን የላቀ አፈፃፀም አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን። "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ሐሙስ:- ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ∙ም አንጸባራቂ ድል ለጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ!! አንጋፋውና… — General Wingate Polytechnic college-Official channel — TG.ME
August 20, 2026 5.1K 4