መንገድ ላይ የቀሩት ተማሪዎች‼️
ከግንቦት 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክኒያት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መንገድ ላይ እንዳሉ መንገዱ ተዘግቶባቸው ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠዋል።
መንገድ ተዘግቶባቸው ከቤተሰቦቻቸው ሳይደርሱ ከቀሩት ውስጥ 234 የወልደያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
ከወልደያ ተነስተው ጋይንት፣ደበረታቦር፣ወረታ ፣ባህርዳር፣ጎንደርና በዙሪያ ወደ ሚገኙ ቦታዎች እየተጓዙ ያሉ ተማሪዎች ሰሜን ወሎ ዞን ፍላቂት ገረገራ ከተማ፡ሲደርሱ መንገድ ተዘግቶባቸው በከተማው ለመቆየት ተገደዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አንደበት ተስፋየ የአካባቢውን ህብረተሰብ፣ ወጣት፣የመናሃሪያ አስተባባሪዎችን፣በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችን፣ሹፌሮችን፣እድሮችንና ነጋዴዎችን በማስተባበር ምግብና መጠጥ አዘጋጅቶ ተማሪዎችን እየተንከባከቡ ይገኛል።
# በከተማው የሚገኙ አልጋ ቤቶች ለተማሪዎች በነጻ አልጋቸውን ሰጥተዋል።
# የአካባቢው ወጣቶች ለመጠጥና ንጽህና መጠበቂያ ውሃ ለተማሪዎች እያቀረቡ ይገኛል።
# ወጣቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ እንጀራ እያዋጣና ወጥ እየሰራ ተማሪዎችን እየመገበ ይገኛል።
# የሃይማኖት አባቶች ደግሞ በቦታው ተገኝተው ጾለትና ቡራኬ እየሰጧቸው ይገኛል።
# ዛሬ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የሰኔ ጾም የሚገባበት በመሆኑ ትናንት የጾም መያዥያ ለክርስቲያን ተማሪዎች ፍየል ታርዶላቸዋል።
# ለሙስሊም ተማሪዎችም ለብቻቸው ፍየል ታርዶላቸዋል።
ተማሪዎቹ ከቤተሰብ ቢርቁም በፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ ግን የጎደለባቸው ነገር የለም ሲሉ የፍላቂት ገረራ ከተማ ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ለዚህ በጎ ተግባር ለፍላቂት ገረራ ከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።
(አዩዘሀበሻ)
=====================
💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s








