በጊምቢ እና ቢላ መስመር በርካታ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው ተሰማ። 📌አሽከርካሪዎቹ ታግተዋል ነው የተባለው… — Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ — TG.ME

በጊምቢ እና ቢላ መስመር በርካታ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው ተሰማ።

📌አሽከርካሪዎቹ ታግተዋል ነው የተባለው

​በኦሮሚያ ክልል ጊምቢ እና ቢላ መስመር በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት በርካታ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን እና አሽከርካሪዎች መታፈናቸው ተገለፀ።

​ድርጊቱ የተፈጸመው በጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፣ በጥቃቱ ሳቢያ በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱ ታውቋል።እስካሁን ከመንግስት አካል የተሰጠ መረጃ የለም።

በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ ባለድርሻ አካላት እንደጠቆሙት፣ በአሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸመው እንግልት፣ የንብረት ውድመት እና የህይወት መስዋዕትነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ እየተባባሰ መጥቷል።

​ችግሩ በአሽከርካሪዎች ደህንነት እና በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ደቀነው ስጋት የከፋ በመሆኑ፣ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ለአካባቢው ጸጥታ አፋጣኝ እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡ አሳስበዋል።
#Wasu_Mohammed
👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇
https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
😭47❤45🕊9😢5👍2🥰1
September 9, 2026 19.2K 29