መረጃ ላለፉት ዘጠኝ አመታት ህዝብን ሲያገለግል የቆየ ተቋም ነው፡፡ ከዚህ በታችን የምታይዋቸው ሜዲያዎች በነጻ ዝግጅቶቻቸውን በአየር ላይ በቀጥታ በሳተላይት ያሰራጫሉ፡፡ ከነዚህ ሜዲያዎች መካከል ሶስቱ በአገር ቤት ፋኖዎች መካከል ሆነው የፋኖን እንቅስቃሴ የሚደግፉ ናቸው፡፡
መልሕቅ ሜዲያ ውስጥ የሚሰሩት በዋናነት ሸዋ ነው ያሉት፡፡ አሻራ ሜዲያ በዋናነት በጎጃም ነው ያሉት፡፡ እነ ጌትነት አሻግሪ ፣ መረብ ሜዲያ በዋናነት ወሎ ነው ያሉት፡፡ እንደዚያም ሆኖም ግን እነዚህ ሜዲያው ሌሎች ጠቅላይ ግዛት ያሉ እንቅስቃሴዎችን በስፋት ከዚያው ከአገር ቤት ይዘግባሉ፡፡
ሌላው እዚህ ላይ ያልተጠቀሰው፣ በፋኖ አደረጃጀቶች የህዝብ ግንኙነት ክፍል፤ የሚላቁ፣ ክለህዝብ ግር ስብሰባዎች ሲያደርጉ፣ ወታደራዊ ምርቃቶች ሲፈጽሙ፣ የመስክ ቃለ መጠይቆች በቀጥታ ሲልኩ፣ በሰበር ዜና በመረጃ ቲቪ ለህዝብ ይሰራጫል፡፡
እዚያው ከጎንደር ፋኖዎች ጋር ሆነው፣ የጎንደር ፋኖዎች እንቅስቃሴ የሚያቀርቡ ወገኖች ካሉ እነርሱንም እናስተናግዳለን፡፡ ከዚህ በፊት እንደምናደርገው ሁሉ ለጎንደር ህዝብ በቀጥታ መልእክቶቻቸው እንዲደርሱ እናደርጋለን፡፡
