ተወዳጆች ሆይ
እንደ ኃጢያቴና እንደ በደሌ ብዛት ቢሆን ኖሮ ከደጁ እጅግ የራቅሁ፡ ከፊቱም የተጣለሁ ነበርኩ።
እኔ በሚያጎድልና በመንገራደድ በሚበዛው ሕይወቴ ውስጥ ስንከራተት፣ የእርሱ አባትነትና ምሕረት ግን አንድም ቀን አልተለየኝም።
ገፍቶ ከቤቱ አላስወጣኝም እንደኔ ኃጢያት፤ ይልቁንስ ይቅር ባይነቱን አልብሶኝ፣ በፍቅሩ ጥላ ሥር ከልሎኝ ዛሬም በደጁ እንድቆም አደረገኝ።
የኃጢያቴን ጥልቀት ሳይሆን የእርሱን የይቅርታ ታላቅነት አይቶ አልፎኛል።
ይህ የእርሱ ቸርነት እጅግ ድንቅ ነው! ሁልጊዜም በፊቱ እንድንበረከክና ለአባታዊ ፍቅሩ በምስጋና እንድንሞላ የሚያደርግ የማይነጥፍ ምሕረት።
አምላካችን ሆይ እባክህ ማረን🙏🙏🙏
✍️ / ዑራኤል

3August 31, 2026 252 3