ተወዳጆች ሆይ! ​ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ እንዲህ ሲሉ ያስተምሩናል፡ ​“ለማንም… — ተግሳጽ — TG.ME

ተወዳጆች ሆይ!

​ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ እንዲህ ሲሉ ያስተምሩናል፡

​“ለማንም አልታዘዝም የሚል ሰው፣ በእርግጥ ለራሱ ትዕቢትና ኩራት እየታዘዘ ነው!”


​— አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ +

​እውነተኛ ነፃነት በራስ አስተያየት ላይ ብቻ መንጠልጠል ሳይሆን፣ ትህትናን ተጎናጽፎ የሰዎችን በጎ ምክርና ተግሣጽ መቀበል ነው።

ራሱን ከሰው ሁሉ በላይ አድርጎ “የእኔ መንገድ ብቻ ነው ትክክል” የሚል ሰው፣ ነፃ ወጥቻለሁ ብሎ ቢያስብም በሐቅ ግን የራሱ እኔነትና ኩራት ባሪያ ሆኗል።

​እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንንም ከትዕቢት መንፈስ ጠብቆ፣ በትህትና ፍቅርና መታዘዝ እንድንመላለስ ልቦናችንን ያብራልን!

✍️ / ዑራኤል


ማንኛውም ሀሳብ
👇👇👇
@Mogesinewokibrene
❤3
September 1, 2026 736 4