እንደ እድል ሆኖ ያደግኹት በመልአኩ ቤት ነው። ስለ እርሱ በቃል የማይገለጽ ልዩ ፍቅር አለኝ። በሄድኩበት ሁሉ… — ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️ — TG.ME

እንደ እድል ሆኖ ያደግኹት በመልአኩ ቤት ነው። ስለ እርሱ በቃል የማይገለጽ ልዩ ፍቅር አለኝ። በሄድኩበት ሁሉ ስሙ ሲጠራ ከሰማኹ አንዳች የደስታ ስሜት ሰውነቴን ውርር ያደርገዋል። "ሚካኤል" ብዬ ያልቀለለ ሸክም፣ ያልተመለሰ ጸሎት የለኝም። አንዳንዴ መልአኩ በጣም ቅርቤ ይመስለኛል። ደግሞ ስለ እርሱ ሳስብ ያሳዝነኛል። ለምን? እንጃ ግን ለእኔ ስለሚያዝንልኝ ይሆናል። ስለ እኔ የሚጨነቅ፣ የሚሳሳልኝ ይመስለኛል። ስለዚህ ያሳዝነኛል። ሚካኤል የዋህ፣ ትሑት፣ ሰውን ወዳጅ መልአክ ነው። ሁልጊዜ ሲዘመር ደስ የሚለኝ መዝሙር አለ
•‎•
👉 ነዋ ሚካኤል መልአከክሙ
      ይስአል ለክሙ በእንተ ምሕረት
ትርጉም:- " እነሆ ሚካኤል መልአካችሁ ምሕረትን ይለምንላችሁ "
•‎•
👉 ሚካኤል መልአኬ ፣ ሚካኤል መልአካችን!
•‎•
ከታናሽነቴ ጀምሮ እኔን የመገበኝ፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው!
•‎•
መልካም የጾም !
❤8👍1👏1
February 19, 2026 1.4K 2