👉🏼 እንኳን ለዳግም ትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ‼️
••
ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት ( ሁለተኛ መነሳት )
••
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ " ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል። ሁለተኛ ለምን ተገለጠ?
••
👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን
••
የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል።
••
ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል። ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ። ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች ( የዳሰሰች ) እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች። እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ።
3April 27, 2025 2.4K 4