‹‹ ቤዛ ›› ማለት ምን ማለት ነው? እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም ቤዛ ትባላለችን ?
ብዙ ጊዜ ድንግል ማርያም እንዴት ቤዛ ትባላለች ? ይላሉ ፤ በእርግጥ ግን እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም የአለም ቤዛ ናት ።‹‹ ቤዛ ›› በቁሙ ሲተረጐም ዋጋ አለው ወይም ጥቅም አለው ማለት ነው ። እንዲሁም ቤዛ የሚለው ቃል "ቤዘወ"፦ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ቤዛ በቁሙ ሲተነተን እንዲህ ማለት ነው ። ዋጋ ፣ ካሳ ፣ ለውጥ ፣ ምእትክ ፣ ሀላፊ ፣ ዋቢ ፣ ዋሥ ፣ መድኅን ፣ ተያዥ ፣ ጥላ ፣ ጋሻ ... ማለትነው ።ቤዛ በደቂቅ አገባብ ሲፈታ ደግሞ ሥለ ፣ ፋንታ፣ ምክንያት የሚሆንተብሎም ይተረጐማል ።
•••
አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ መፅሐፍ ሠዋሠው ውግሥ በመዝገበ ቃላት ሐዲሥ 1948 ዓ ም ገፅ 266፡፡ ወይምደግሞ በሌላ መንገድ ከሣቴ ብርሐን ተሠማ መፅሐፋቸው ቤዛ ሲተረጉሙ እንዲህ ብለው አሥቀምጠውልናል ለውጥ ፣ ካሣ ፣ ወይም ደግሞ በአንድ ሠው ላይ መከራና ሞት ተላልፎ መሞትማለት ነው ወይም ታደገኝ ወይም ምትክ ሆነኝ ማለት ነው ወይም ደግሞ ለመከራ ለሞት ለወጠኝ ማለት ነው ወይም ቤዛ ሆነኝ ማለትነው ። የበለጠ ለመረዳት አልያም ቤዛ ሥለሚለው ቃል በደንብ ለማወቅ እነዚህን መፅሐፍቶች መመልከት ይቻላል ።
•••
እንደዚሁም ቤዛ የሚለው ቃል ፦ ካሣ ፣ የደም ቤዛ ፣ አንዱ ሠው የሠውንደም ሥለሚያፈሠው ለውጥ ወይም ዋጋን ፣ ገንዘብን ፣ ካሣን መሥጠት ወይም መዋጀት ማለት ነው ።ከሣቴ ብርሐን 1951 ዓ.ምገፅ 532 ድንግል ማርያምን ስለምን የአለም ቤዛ እንላታለን? የእመቤታችን ቤዛነትም ከላይ በተረዳነው መሠረት ቤዛ ከሚሉት የትርጓሜ ቃላት መካከል ምትክ ፣ ዋሥ ፣ ምክንያት ... ከሚሉት መካከል ምትክ የሚለውን ስንወስድ ድንግል ማርያም የህይዋን (ሔዋን) ምትክ በመሆኗ ነው ፤ ‹ምክንያት› የሚለውን ስንወስድ ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም ለኛ መዳን ምክንያት ስለሆነች ነው። እግዚአብሔር ለአለም መዳን በድንግል ማርያም ታላቅ ስራን አድርጉአልና ቤዛዊት ዓለም እንላታለን። የድንግል ማርያም በእምነት መታዘዝ ለዓለም መዳን ምክንያት ሆናለች። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ስለተቤዤ ቤዛዊት ዓለም እንላታለን።
•••
ቤዛ የሚለው ቃል ለሙሴም ተሰጦት እናነባለን። ( የሐዋ ሥራ 7:35) በመልአክ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።እንግዲህ ይህ የፍጡር ቤዛነት የእግዚአብሔርን ቤዛነትይሽራልን? አይደለም፡፡ እንዲያውም ቸር እግዚአብሔርለወዳጆቹ የሚሰጠውን የባለሟልነት ስጦታ ብዛት ይገልፃልእንጂ፡፡ ሙሴ ወገኖቹን ከመጥፋት እንደምን አዳናቸው ( ተቤዣቸው )( ታደጋቸው )? እንደክርስቶስ ደሙን በማፍሰስ ነውን? አይደለም በእግዚአብሔር ዘንድ ‹ይህን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው ፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍኽ እባክኽ ደምሰሰኝ› በማለትየተወደደፀሎቱን በማቅረብእንጂ ( ዘጸ.32፤32 )፡፡
•••
ዳዊትም ‹ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም ኖሮ ›› ሲል የገለፀው ይሄንኑ ነው፡፡ስለዚህም መጽሐፍ የፃድቅ ሰው ፀሎት በስራዋ እጅግ ሃይልን ታደርጋለች ይላል፡፡የእመቤታችንና የድንግል ማርያም ቤዛነት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርሥቶስ ቤዛነት ጋር ያለው ልዩነትእጅግ የሚራራቅ ነው ።ጌታችን በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው ። እንዲሁም በደሙ ዋጅቶ በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው። ቤዛ ማለትእራሥን ሥለሌሎች አሣልፎ መስጠት ማለት ሥለሆነ ጌታችንም ሥለበጐቹ እራሱን አሣልፎ ሠጥቷል ሆኖም የአለም ቤዛ ነው ። ታዲያ የአለምቤዛ ክርስቶስ ከሆነ ድንግል ማርያምስ ቤዛዊት አለም መባሏ ስለምን ነው ቢሉ፦ ክርስቶስ አለምን ሁሉ ከሞት ወደህይወት ያሻገረበት፣ ሃጢአታችንን ሁሉ የደመሰሰበት ፣ የሚደመስስበትም ክቡር ደሙ ፣ ቅዱስ ስጋው ከእመቤታችን ስለነሳው ነው ፤ በዚህም ክርስቶስ ከመወለዱ አንስቶ በቤተልሄም የከብት ግርግም ተጀምሮ፡ በግብፅ ስደቱ በቀራኒዮ ስቃዩና ሞቱ ሁሉ አብራው አለችና በክርስቶስ የድህነት ስራ ውስጥ የእመቤታችን ስራ ጉልህ ሆኖ ይታያልና ነው፡፡ለማጠቃል ያክል፡- ሙሴ ምክንያት ሆኖ ነጻ ያወጣቸው ለጥቂት ነገዶች ወይም ‹ለእስራኤላውያን› ብቻ በመሆኑ ‹‹ቤዛ›› ብቻ ተብሏል፡፡
••
ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ግን ምክንያተ ድኅነት ሆና ነጻ ያወጣችው ‹ዓለም ሙሉ›ስለሆነ (ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ተሰቅሏልና) ‹‹ቤዛዊተ ዓለም›› ትባላለች፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን ለቅዱሳንም በጸጋ ተሰጥቷል፤ በመጸሐፍየጸጋ አምላክነት ለቅዱሳን ተሰጥቶ እናያለን ‹እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦እይ፥እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌኻለኹ›፤ ክርስቶስየዓለም ብርሃን እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ቅዱሳንንም ‹እናንተየዓለም ብርሃን ናችኹ› በማለት በጸጋ የዓለም ብርሃን እንደሚባሉ መጽሐፍ ምስክርነው ( ዘጸ7፤1 ማቴ 5፤14) የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲህ ነዉ ፤ ክብርና ምሥጋና ለቤዛዊት አለም ለእመቤታችን ለቅድሥት ድንግልማርያም ይሁን አሜን።
•••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
10
2April 21, 2025 2K 11