በመጸሐፍ ቅዱስ ቤዛ ማነው? ቃሉ የዋለው ለኢየሱስ ብቻ ነው ? ወይስ እንደ አገባብ ይተረጎማል? ••• 1ኛ… — ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️ — TG.ME

በመጸሐፍ ቅዱስ ቤዛ ማነው? ቃሉ የዋለው ለኢየሱስ ብቻ ነው ? ወይስ እንደ አገባብ ይተረጎማል?
•••
1ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ ብር ቤዛ ነው
“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው ፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።”ዘጸአት 30፥12
•••
2ኛ- በመጽሐፍ ቅዱስ ሀብት ቤዛ ነው
“ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።” ምሳሌ 13፥8
•••
3ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ ኅጥእ እና በደለኛ ሰው ቤዛ ተብሏል “ ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው ፤ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።” ምሳሌ 21፥18
•••
4ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ አገር ቤዛ ተብሏል “ እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።” ኢሳይያስ 43፥3
•••
5ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ መሪ ቤዛ ተብሏል
“ ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን ፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው። ”
ሐዋርያት 7፥35
•••
6ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ ቀን ቤዛ ተብሏል “ ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ”  ኤፌሶን 4፥30
•••
👍1
April 21, 2025 2.2K 7