የነቢያችን_ሰለሏሁ_ዐለይሂ_ወሰለም_የአመጋገብ ሱና
✏️➊➭ ነቢያችንﷺ ከምግብ በፊት ይታጠቡ ነበር።
✏️➋➭ ነቢያችንﷺ ተደግፈው በልተው አያውቁም። ለምግብ ሲቀመጡ ወይ ተሸሁድ ላይ አይነት፣ ወይም እንዲሁ ተቀምጠው አንድ እግራቸውን ጉልበት ደረታቸው ላይ በማቀፍ ወይ ደግሞ ቁጢጥ በማለት ነበር።
✏️➌➭ ነቢዩﷺ ምግብ ሲጀምሩ ቢስሚላህ ወአላ በረከቲላህ በማለት ነው።
✏️➍ ➭ነቢያችንﷺ ምግቡን ካልወደዱት ስለምግቡ ምንም ሳይናገሩ መመገብ ይተው ነበር።
✏️➭ የማያውቁት ምግብ ከገጠማቸው አስቀድመው ስለምግቡ ይጠይቁ ነበር።
✏️➏ ➭ነቢያችንﷺ ምግባቸውን አሽትተው አያውቁም። ጥሩ ያለሆነ ልምድ እንደሆነም ይቆጥሩታል።
✏️➐ ➭በጣም የሞቀ ምግብ አይመገቡም ያቀዘቅዙት ነበር። «አላሁ ተዐላ እሳት አይመግበንም» ይሉ ነበር። በጣም የሞቀ ምግብ ውስጥ በረካ የለውም ብለዋል።
✏️➑➭ ነበዩﷺ ምግብም ሆነ መጠጥ ላይ ተንፍሰው አያውቁም። መጠጥን በትንፋሽ ማቀዝቀዝ አይወዱም ነበር።
✏️➒ ➭ነቢዩﷺ ሀብታሞች ቤት እንደሚሆነው በብዙ ሳህን የሚቀርብ ምግብ አይወዱም ነበር።
✏️➓ ➭በአብዛኛው ነቢዩﷺ ሲመገቡ በሶስት ጣታቸው (አውራ፣ ጠቋሚና መሐል ጣታቸውን) በመጠቀም ሲሆን ምግቡ ቀጠን ያለ ከሆነ ቀለበት ጣታቸውን ይጨምሩ ነበር።
✏️➊➊➭ አንድ አይነት ምግብ ከቀረበላቸው ከፊታቸው ይመገባሉ የተለያየ አይነት ከሆነ ግን ከሌላ ቦታ ከመመገብ አይቆጠቡም ነበር።
✏️➊➋ ➭ነቢዩﷺ ከሰው ጋር እየበሉ ከሆነ የሚነሱት በመጨረሻ ነበር። ቀስ ብለው የሚመገቡ ሰዎችን ላለማሳፈር።
✏️➊➌➭ ሲጨርሱ ጣታጫውን በአፋቸው ያፀዱ ነበር።
✏️➊➍➭ ነቢዩﷺ ተመግበው ሲጨርሱ እንዲህ ይሉ ነበር👇👇👇
«الحمد الله الذي أطعم وسقى وسوغه و جعل له مخرجا»
✏️➊➎➭ ነቢዩﷺ ምግብ ለተሰባሰቡ ሰዎች የሚያከፋፍሉ ከሆነ በቀኝ ይጀምሩ ነበር። በግራ መጀመር ከፈለጉ በቀኝ ያለውን ያስፈቅዱ ነበር።
✏️➊➏ ➭ነቢያችን ﷺ ስጋ ወደ ቤት ሲያመጡ ጎረቤት እንዲበቃ ተደርጎ እንዲሰራ ያደርጉ ነበር።
✏️➊➐➭ ነቢዩ ﷺ ሀለዋ፣ ማር፣ ኮምጣቴ፣ ተምር፣
ሀብሀብ፣ ኪያር እና ዝኩኒ ይወዱ ነበር።
📲 ለሌሎችም ሼር በማድረግ የነብያችንን ሱና እናሳውቃለን👌
┄┄┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉┄
┄┄┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉┄
#صلوا_على_النبيツ #ኸሚስ
#ጁመዓ
T.me/tebligda
Telegram
ዳዕዋ እና ተብሊغ - Da'wah and Tabligh
ዳዕዋ እና ተብሊግ - Da'wah and Tabligh ስለ ዳእዋ ወተብሊغ የምንማርበት እና ኢስላማዊ የሆኑ መረጃዎችን የምናገኝበት ፔጅ ነዉ

6
1December 5, 2024 2K 18