🔳DAILY HADITH🔳
(Part 279) #hadith279
"ኣቡ ሰኢድ ኢብን ማሊክ ኢብን ሲናን ኣል ኹድርይ ረዲ ኣላሁ ኣኑሁ እንዳስተላለፉት የኣላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ኣሌሁም ወሰለም እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ።
"ከእናንተ በፊት በነበረው ዘመን ኣንድ የዘጠና ዘጠኝ ሰዎችን ነፍስ ያጠፋ ሰው ነበር። ምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይበልጥ ኣዋቂው ማን እንደሆነ ጠየቀ ። ወደ ኣንድ መናኛ ኣመላከቱት። ከእርሱ ዘንድ ሄደ ። ዘጠና ዘጠኝ ነፍስ እንዳጠፋና ተውበት ቢያደርግ
ተቀባይነት ያገኝ እንደሆነ ጠየቀው ።"ኣታገኝም " ኣለው መናኙ።ገደለውና መቶ ሞላው ።ከዚያም ምድር ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይበልጥ ኣዋቂው ማን እንደሆነ ጠየቀ ።ወደ ኣንድ ኣዋቂ ሰው ኣመላከቱት ። ኣንድ የመቶ ሰዎችን ህይወት ያጠፋ ሰው ተውበት ቢያደርግ ተቀባይነት ያገኝ እንደሆነ ጠየቀው። "ኣዎ! (ተቀባይነት ያገኛል) ፣በእርሱና በተውበቱ መካከል ግርዶ የሚፈጥረው ማን ነው?! እገሌ ወደተባለው ቦታ ሂድ ።እዚያ ስፍራ ላይ ኣላህን ብቻ የሚያመልኩ ሰዎች
ኣሉ። ከእነርሱ ጋር ኣብረህ ኣላህን ኣምልክ።
ወደ ነበርክበትም ኣገር ኣትመለስ ።የክፋት ስፍራ ነውና። "አለው ኣሊሙ።ወደ ተጠቆመውም ሀገር ተጓዘ ።መንገድን እንዳጋመሰ ሞት ነጠቀው።የእዝነት (ጀነት) እና የቅጣት (ኣዛብ) መላእክቶች ተሟዋገቱ። "ቶብቶና ቀልቡን ወደ ኣላህ ኣዙሮ ነው የመጣው ።"ኣሉ የጀነት መላኢኮች ።"በጎ ተግባር ፈፅሞ ኣያውቅም።"ኣሉ የኣዛብ መላኢኮች ።ኣንድ መላኢካ በሰው ተመስሎ ወደ እነርሱ መጣ ።ብይን ይሰጣቸውም ዘንድ ጋበዙት ።"ሁለቱ መሬቶች (የመጣበትንና የሚሄድበት) ከሞተበት ስፍራ ያላቸውን እርቀት ለኩ ።ለቀረበው ወገን ይሆናል። ኣላቸው።ለኩ።መሄ ድ ወደ ጀመረበት ስፍራ ቀረብ ብሎ ኣገኙት ።የጀነት መላኢኮች ወሰዱት።"
(ቡኻሪይና ሙስሊም)
⚪️ Another hadith
https://t.me/sycotube/22158
🔰 use it for your self then share to your friends & get ajir on it.
2
1
1August 30, 2026 447 1