መልካም ሰው ለመሆን ኸይረኛ ሰው ለመሆን ብትፈልግ እንኳን ጊዜው አይመችም። ጥሩ ነገር ማድረግህ እንደ ሞኝነት ሚቆጠርበት ዘመን ላይ ደርሰናል። አንድ አንዴ መልካም ያደረግክለት ሰው እንኳን ሞኝ መስለህ ትታየዋላህ። እኔ መልካምነት ስለ ሰዎች ኸይር ማሰብ እና በሰዎች ሃጃ ላይ መቆም ዋጋ አስከፋይ ቢሆንም እወደዋለው። ትንሽ ጊዜው ሚያስፈራ ይመስላል ኸይር የዋልክለት ሰው ሸንጐ ላይ በዳዬ ነው ብሎም ሊያቀርብህ ይችላል። ስለ ሰው መኖር መልካም ማድረግ እንደ ፋራነት የተቆጠረበት። ስለ ራስ ማሰብ ስልጡንነት የሆነበት ዘመን። ወንድምህ ጓደኛህ የቅርብ ሰው ሙሲባ አጋጥሞት እንዴት እረፍት እንደሚሰጥ አላውቅም።
September 21, 2024 955