ወንድሜ አትውደቅ! አላህ አይፈትነህ መውደቅ ፈተናው ለወደቀው ሰው ብቻ አይደለም ዙሪያው ላይ ላሉትም ሰዎች ነው። መውደቅ ያስፈራል ምንም ባይኖርህ አለመውደቅህ ስኬት ነው ሰው ፊት መቆም ከባድ ነው ላላየው አይድረስበት ላየው አላህ ይፈርጀው። ሰው ፊቴ ሲቆም ቀድሜ መሸማቀቅ ጀምርያለው ብርክ ብርክ ይለኛል። ከዛ ሰው በላይ እሸበራለው መውደቅ በሰው እጅ ላይ ማረፍ ፈተና ነው። እንደው ከቻልን ሰው ሳይቀድመን እንቅደመው አቅም ካለን ሰው ቤታችን አያንኳኳ ለዝየራ ማንኳኳት እና ለክጀላ ማንኳኳት ይለያል።
August 27, 2024 897 3 1