ማህበራዊ ሚዲያዎች ካደረሱብን ከባባድ ጉዳቶች ውስጥ አንዱ ከቁርኣን መራቅ ነው። እስኪ መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ… — S֮t֮r֮o֮n֮g֮ I֮m֮a֮n֮🇵🇸 — TG.ME

ማህበራዊ ሚዲያዎች ካደረሱብን ከባባድ ጉዳቶች ውስጥ አንዱ ከቁርኣን መራቅ ነው። እስኪ መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ቁርኣን ገልጠን ያነበብነው? በምን ያህል ጊዜ ቁርኣን እናኸትማለን? ልባችን ይበልጥ የሚረጋጋው የትኛው ላይ ስንሆን ነው? ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ወይስ ቁርኣን ላይ ስንሆን? በቀን ምን ያህል ጊዜያችንን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እናጠፍለን? እስከ መቼስ ነው በዚህ መልኩ የምንቀጥለው? መንዘላዘላችንን፣ በጊዜያችን መጫወታችንን "በቃ" ልንል እራሳችንን ልናስተካክል ይገባል። በየቀኑ የምንቀራው ቋሚ መጠን (ዊርድ) ሊኖረን ይገባል። በቀን 20 ገፅ እንኳ ብንቀራ አንድ ጁዝእ ማለት ነው። ከ30 ደቂቃ ያልበለጠ ቆይታ። ይሄ ለቁርኣን ይበዛል? በዚህ መልኩ ጠብቀን ብንጓዝ በየወሩ እናኸትማለን። ብርታት ላለው ደግሞ ከዚህ የበዛ ብዙ መፈፀም ይችላል። አላህ በኸይር ላይ ብርታት ይሰጠን።

@strong_iman
❤80💔19👍10
August 29, 2026 3.7K 3 17