የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋጋጥ የሴቶች ክንፍ ሚና የጎላ ነው፦ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ይህን ያሉት የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የ2017 በጀት አመት አመታዊ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 በጀት አመት እቅድ በገመገመበት ወቅት ነው። የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር እንዳሉት በበጀት አመቱ የተሰጡ ተልእኮዎችን በተገቢው ለመፈፀም ሁሉም የድርሻውን ወስዶ በተደረገው ርብርብ የሴቶች ክንፍ ሚናው የጎለ እንደነበር አመላክተዋል። ወቅታዊ ንቅናቄ ተግባርን በተሳለጠ መልኩ መሰራቱን ያተናገሩት ወ/ሮ ነኢማ በዚህም የሰላም እሴቶችን በበጎ ማጎልበት ፣በሌማት ትሩፋት ስራዎች የክንፍ አባላት ስራዎች በስፋት መሰራታቸውን አንስተዋል። የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጀሚላ ኢብራሂም በበኩላቸው በፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች በስልጤ ዞን ሴቶች ክንፍ አባላት በኩል አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። በለፈው በጀት አመት በኢኮኖሚው መስክ በተለይም ከተረጂነት ወደ ምርታማነትና በቁጠባ፣ከማህበራዊ መስክ የትምህርትና የጤና ስራዎች፤የክንፉን አደረጃጀት ማጠናክርና የክንፉን ብልፅግና ህብረትና ብልፅግና ቤተሰቦችን ማጠናከር ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ወ/ሮ ጀሚላ አንስተዋል። https://www.facebook.com/100082825107454/posts/pfbid0u69F4nZrvWPKusnPRUQqsQzWU2wCVJ499pb2wb7hubYgf3jU2bFFzuqspZQWgAYRl/?app=fbl
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋጋጥ የሴቶች ክንፍ ሚና የጎላ ነው፦ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር የስልጤ… — ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6 — TG.ME
August 6, 2025 743