በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ 1ሺህ 800 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ… — ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6 — TG.ME

በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ 1ሺህ 800 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ክህሎት መር አጫጭርና መደበኛ ስልጠናዎችን በመስጠት ፀጋዎችን ወደ ሃብት እንዲቀየሩ በትኩረት መሰራቱን አንስተዋል።

በግምገማው ላይ የተሳተፉት የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ተቋማት ብቁና ውጤታማ አሰልጣኞችንና አመራሮች እያፈራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ግምገማ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በማረም ጥራትና ተደራሽነቱ የተረጋገጠ ውጤት ለማስመዝብ እንደሚያግዝ በመድረኩ ተገልጿል፤

በግምገማ መድረኩ ከሁሉም ክልሎች እና ሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮች ተሳታፊ ናቸው።
August 4, 2025 626