የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ራሳችን ተልመን፣ ራሳችን ሰርተን፣ ራሳችን ጽፈን፣ ራሳችን ለዓለም… — ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6 — TG.ME

የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ራሳችን ተልመን፣ ራሳችን ሰርተን፣ ራሳችን ጽፈን፣ ራሳችን ለዓለም የምንናገረውና የምናሳየው መሆን ይኖርበታልም ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

ለዚህ ደግሞ መንግስት ተቋሙ የጀመራቸውን ሀገራዊና አህጉራዊ የለውጥ አራማጅ ግቦች ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ኢዜአ ከዜና ባለፈ የህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማፅኛ፣ አፍሪካውያን በራሳቸው አስተሳሰብ የራሳቸውን ታሪክ እንዲናገሩ ዋነኛ የትርክት ማሰረጫ መሰረተ ልማት ሆኖ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢዜአ ለጀመረው የለውጥ ስራ በትጋት ለሰሩና ለተባበሩ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
August 4, 2025 511