የእንቁላል ዶሮ በማርባት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸዉን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን በዘርፉ የተሰማሩ ወጣቶች ገለፁ!… — ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6 — TG.ME

የእንቁላል ዶሮ በማርባት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸዉን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን በዘርፉ የተሰማሩ ወጣቶች ገለፁ! የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዩኒት በበኩሉ የሌማት ቱሩፋት ተግባር ጠንካራ ኢኮኖሚን በመገንባት የማህበረሰባችንን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባሻገር የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት ድርሻው የጎላ መሆኑን ነዉ ያስታወቀዉ። በስልጤ ዞን ዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር አለም ገበያ ከተማ የመልጋች መንደር ነዋሪ የሆኑት ወጣት ራህመቶ ከማልና ኑርሰቦ ከማል በከተማዉ የሚስተዋለዉን የእንቁላል ምርት እጥረት ችግር በመቅረፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ ከ 7 መቶ ሺህ ብር በላይ ኃብት በማፍሰስ 1 ሺህ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ማርባት መጀመራቸዉን ገልፀዋል። በከተማዉ ግብርና ዩኒት በተሰጣቸዉ ስልጠናና ምክር ተነሳስተዉ በቅርብ የጀመሩት ስራ ሙሉ በሙሉ ውጤቱን ከጊዜ አንፃር መለካት ባይቻልም ደስተኛ ሆነን እየሰራን ስለሆነ ስራችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያስመዘግብ ተስፋ ሰንቀናል ነዉ ያሉት ወጣቶቹ። https://www.facebook.com/share/p/16jkNr4aEz/

August 22, 2025 1.6K 3