25 ዓመታት በዘለቀ በጎ አድራጎትና ሰብዓዊ አገልግሎት ጉልህ ዐሻራውን ያኖረው ቢላሉል ሐበሺ
*******
ቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ እድር እያከናወናቸው ያሉ በጎ ሥራዎችን ለማስቀጠል በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።
ተቋሙ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ቢላሉል ሐበሺ ባለፉት 25 ዓመታት እገዛ ለሚሹ ወላጅ አልባ ልጆች (የቲሞች)፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ እናቶች እና ሌሎች ወገኖች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ድጋፍ በመስጠት ጉልህ ዐሻራ ማኖሩ ተገልጿል።
ተቋሙ በሩብ ምዕተ ዓመት ቆይታው ከ10 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ወላጅ አልባ ህፃናት እና ወጣቶች የትምህርት እና የሕክምና ድጋፍ ማድረጉን የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ገልፀዋል።
በተመሳሳይ ለ1 ሺህ 500 አረጋውያን ድጋፍና እንክብካቤ፣ ለ1 ሺህ 500 ወጣቶች እና ሴቶች የማቋቋሚያ ድጋፍ ተደርጓል ተብሏል።
https://www.facebook.com/100082825107454/posts/pfbid0H9kwRS4EDzCqvYFpTnzmNoLzym2cdHsEUsAr8kLoRpEhdpPU1nMDBb8DMBDGCWeKl/?app=fbl

August 6, 2025 1.2K