የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ከፑቲን ጋር ለመነጋገር ሞስኮ ገብተዋል
***
ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ ሞስኮ የገቡት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያስቀመጡት የተኩስ አቁም ስምምነት ቀነ ገደብ ከማብቃቱ 2 ቀናት አስቀድሞ ነው።
ዊትኮፍ ወደ ሞስኮ ያቀኑት በሩስያና ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመነጋገር መሆኑንም ነው የተገለጸው።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩስያ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ካልፈረመች ከባድ ማዕቀብ ይጠብቃታል ሲሉ ዛቻ የተሞላበት ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን የተኩስ አቁም ስምምነቱን እስከ አርብ ድረስ ካልፈረሙ በሩስያ የነዳጅ ታንከሮችና መርከቦች ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል መዘጋጀታቸውን ነው ትራምፕ የገለጹት።
https://www.facebook.com/100082825107454/posts/pfbid02qLbTccbYLhEJAomBjasbHqP4o9rxasG5F9Tta2eWArZh9Ye6BjNy9feJBA3LRZKMl/?app=fbl

August 6, 2025 828