በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ለመሆን እየተሰራ ነው በቴክኒክና ሙያ ስልጠና… — ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6 — TG.ME

በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ለመሆን እየተሰራ ነው በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ለመሆን እየተሰራ መሆኑን የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የተያዘው በጀት አመት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ በድሬዳዋ እያከናወነ ይገኛል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ለመሆን እየተሰራ ነው። በተጠናቀቀው በጀት አመት የሀገርን የብልጽግና ጉዞ ማሳካት የሚያስችሉ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችንና በክህሎታቸው የበቁ ባለሙያዎችን ማፍራት ተችሏል ነው ያሉት። በተጨማሪም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በማኑፋክቸሪንግ እና በአመራር የትምህርተ ዘርፎች የሶስተኛ ድግሪ ስልጠና መርሃ ግበር መጀመሩን ተናግረዋል። መንግስት ለቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ ክህሎት መር ስልጠናና ዕውቀት የታጠቁ ባለሙያዎች በጥራትና በብዛት ማፍራት አስችሏል ነው ያሉት።

August 4, 2025 659