225 ሺህ የዓሳ ጫጩቶች ወደ ጣና ሐይቅ… 225 ሺህ የቀረሶ ዓሳ ጫጩቶች ወደ ጣና ሐይቅ ተጨምረዋል አለ… — ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6//Siltie FM 92.6 — TG.ME

225 ሺህ የዓሳ ጫጩቶች ወደ ጣና ሐይቅ… 225 ሺህ የቀረሶ ዓሳ ጫጩቶች ወደ ጣና ሐይቅ ተጨምረዋል አለ የባሕር ዳር ዓሳና ሌሎች የውሃ ውስጥ ሕይወት ምርምር ማዕከል፡፡ የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ እርቅይሁን አስማር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷በጣና ሐይቅ ያለውን የዓሳ ሃብት ይበልጥ ለማሳደግ የተሻሻሉ የዓሳ ዝርያዎችን ወደ ሐይቁ የመጨመር ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡ አሁን ላይ እየቀነሰ የመጣውን የዓሳ ሃብት ለማጠናከርና የሕብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡ በምርምር የተሻሻሉ የዓሳ ዝርያዎችን በማባዛት የዓሳ ጫጩቶችን ወደ ጣና እና ሌሎች ውሃማ አካላት የመጨመሩ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ በ2017 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የዓሳ ጫጩቶች መባዛታቸው ጠቅሰው÷ ከዚህ ውስጥም የዛሬውን ጨምሮ 312 ሺህ በላይ የቀረሶ ዓሳ ጫጩቶች ወደ ጣና ሐይቅ ተጨምረዋል ነው ያሉት፡፡ ቀሪው የዓሳ ጫጩትም ወደ አርሶ አደሩ ኩሬና ልዩ ልዩ የውሃማ አካላት ከመሰራጨቱ ባለፈ ለምርምር አገልግሎት መዋሉን አስገንዝበዋል፡፡

August 4, 2025 420