ንብረት ሲገዙ እና ሲሸጡ የሚመለከቱዎት 2 ዋና ታክሶች ንብረት ሲገዙ ወይም ሲሸጡ Property Tax እና… — Sheger Press️️ — TG.ME

🏠 ንብረት ሲገዙ እና ሲሸጡ የሚመለከቱዎት 2 ዋና ታክሶች

ንብረት ሲገዙ ወይም ሲሸጡ Property Tax እና Capital Gain Tax አንድ አይደሉም።

1. Property Tax 🏠

Property Tax ንብረት በባለቤትነት ስለያዙ የሚከፈል ዓመታዊ ታክስ ነው።

በተሰጠው ምሳሌ፦

* የንብረት የገበያ ዋጋ፦ 20,000,000 ብር
* 25% የግብር መሠረት፦ 5,000,000 ብር
* የProperty Tax ምጣኔ፦ 0.5% ቢሆን
* የዓመቱ ታክስ፦ 25,000 ብር

ስለዚህ ንብረት ሲገዙ የግዢ ዋጋውን ብቻ ሳይሆን የባለቤትነት ታክስንም ግምት ውስጥ ያስገቡ።

2. Capital Gain Tax 💰

Capital Gain Tax ደግሞ ንብረትዎን ሲሸጡ ከሚያገኙት የካፒታል ትርፍ ጋር የሚያያዝ ታክስ ነው።

ምሳሌ፦

* ንብረቱን 10 ሚሊዮን ብር ገዙ።
* በኋላ 15 ሚሊዮን ብር ሸጡት።
* የተገኘው ትርፍ፦ 5 ሚሊዮን ብር
* በ15% ከተተመነ፦ 750,000 ብር

ማለትም ንብረት ሲሸጥ የሚገኘውን ትርፍ በማስላት ላይ Capital Gain Tax ይመለከታል።

በአጭሩ

🏠 ንብረት መያዝ → Property Tax

💰 ንብረት ሸጦ ትርፍ ማግኘት → Capital Gain Tax

ንብረት ለመግዛት ዋጋውን ማወቅ ብቻ አይበቃም፤ በግዢ፣ በባለቤትነት እና በሽያጭ የሚመጡ የታክስ ጉዳዮችንም መረዳት ያስፈልጋል።
❤6👏4👎3
September 3, 2026 1.6K 3 16