295 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዷል‼ ​ ኢትዮ ቴሌኮም “ቀጣዩ አድማስ ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር… — Sheger Press️️ — TG.ME

295 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዷል

ኢትዮ ቴሌኮም “ቀጣዩ አድማስ ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር 2028” የተሰኘውን የሶስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታውን ሁለተኛ ዓመት (የ2019 በጀት ዓመት) አጠቃላይ የቢዝነስ እቅድ ይፋ አድርጓል።

📌​በእቅዱ የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
💰 የገቢ እና የውጭ ምንዛሪ ግብ
​አጠቃላይ ገቢ፦ የ36.7% (የ79.2 ቢሊዮን ብር) እድገት በማስመዝገብ 295 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዷል።

​የውጭ ምንዛሪ፦ 253.7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።

📌👥 የደንበኞች ቁጥር እድገት
​አጠቃላይ ደንበኞች፦ በ6.7% በማሳደግ 96.2 ሚሊዮን ለማድረስ፤

​የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች፦ የሞባይል ዳታ እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በ16.5% በማሳደግ 60.01 ሚሊዮን ለማድረስ ግብ ተይዟል።

📌📱 የቴሌብር እና የዲጂታል ፋይናንስ እድገት
​የቴሌብር ደንበኞች፦ 67.69 ሚሊዮን ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

​የግብይት መጠን፦ የንቁ ግብይቶች መጠን 7.4 ትሪሊዮን ብር (በብዛት 4.99 ቢሊዮን) ይደርሳል ተብሏል።

​አነስተኛ ብድር፦ በቴሌብር የሚሰጠው የዲጂታል አነስተኛ ብድር ከ19.51 ቢሊዮን ብር ወደ 35.04 ቢሊዮን ብር ከፍ ይላል።

📌📡 የመሰረተ ልማት እና የኔትወርክ

​የ4G ኔትወርክ፦ 5,417 አዳዲስ የ4ጂ ጣቢያዎችን በመገንባት ሽፋኑን ከ82.23% ወደ 95% ለማሳደግ ታቅዷል።

​የ5G አገልግሎት፦ ተደራሽ የሚሆንባቸውን ከተሞች ቁጥር ከ33 ወደ 73 በማሳደግ የጣቢያዎቹን ቁጥር 648 ለማድረስ ዝግጅት ተጠናቋል።

📱 ስማርት ስልኮች እና የአገራዊ ልማት ድጋፍ
​"ዘኔክሰስ" ስማርት ስልኮች፦ ዲጂታል አካታችነትን ለማረጋገጥ 1 ሚሊዮን ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ስልኮች ለገበያ ያቀርባል።

​የመንግስት ገቢ፦ 43.1 ቢሊዮን ብር የትርፍ ክፍፍል እና 83.8 ቢሊዮን ብር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ግብር ገቢ ለማድረግ ማቀዱን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በስካይላይት ሆቴል ለህዝብ ይፋ አድርገዋል።
❤8🤯8👎3👍2
September 3, 2026 3.3K 10