እየተጠናከረ የመጣው ኤል ኒኖ ከባድ የአየር ሁኔታ ስጋት እያሳደረ እንደሆነ ተገለጸ የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት… — Sheger Press️️ — TG.ME

እየተጠናከረ የመጣው ኤል ኒኖ ከባድ የአየር ሁኔታ ስጋት እያሳደረ እንደሆነ ተገለጸ

የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት እንደገለጸው አሁን ላይ እየተስተዋለ የሚገኘው  የኤል ኒኖ ክስተት በ70 ዓመታት ውስጥ ከታዩት በጣም ኃይለኛ ክስተቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ያስታወቀ ሲሆን፥ ክስተቱም ቢያንስ እስከ የካቲት 2027 ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዓለም ከፍተኛ የአየር ሁኔታ አደጋ ወደሚበዛበት ደረጃ እየገባች መሆኑን አንስተው፥ ኤል ኒኖ እየጠነከረ በመምጣቱ የድርቅ፣ የጎርፍ፣ የመሬት ናዳ እና የከፍተኛ ሙቀት አደጋዎች ሊባባሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

በፓሲፊክ ውቅያኖስ ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ክፍል የባሕር ሙቀት በቅርብ ወራት በከፍተኛ ሁኔታ  የጨመረ ሲሆን፥በተለይም የባሕር ወለል ሙቀት ከመደበኛው በ2 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል ።

የኤል ኒኖ ተጽዕኖ በሰው ልጅ ከሚመነጨው የረጅም ጊዜ የአየር ንብረት ሙቀት መጨመር ላይ ተደምሮ የከፋ የአየር ሁኔታ ሊያስከትል እንደሚችል ሳይንቲስቶች ገልጸዋል።

ባለሙያዎች በበኩላቸው የኤል ኒኖ ተጽዕኖ በሰዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ የሕክምና ድጋፍና የአደጋ ዝግጅት ሥርዓቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
❤7🙏6
September 3, 2026 4.2K 1