በኔፓል በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከዘጠኝ ቀን ፍለጋ ቡሀላ ሁለት ሰዎች በህይወት ተገኙ፡፡ በኔፓል በድንገተኛ… — Sheger Press️️ — TG.ME

በኔፓል በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከዘጠኝ ቀን ፍለጋ ቡሀላ ሁለት ሰዎች በህይወት ተገኙ፡፡
 

በኔፓል በድንገተኛ ጎርፍ ምክንያት በዋሻ ውስጥ ለዘጠኝ ቀናት ተይዘው የነበሩ ሁለት የውሃ ኃይል ማመንጫ ሠራተኞች በሕይወት መገኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በኔፓል በደረሰው አስከፊ የጎርፍ አደጋ ከ አንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉና ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እስካሁን አለመገኘታቸው የሚታወስ ነው።

ሳንጃያ ሻህ እና ካቢር ማሃርጃን ከትሪሹሊ 3A የኃይል ማመንጫ ዋሻ ውስጥ በአዳኝ ቡድኖች የተገኙ ሲሆን፣ በእጅና በእግራቸው ጉዳት ቢደርስባቸውም አምቡላንስ ወደ ካትማንዱ ሆስፒታል ተወስደዋል።

በዚያው ዋሻ ውስጥ ወደ 40 የሚጠጉ ሰዎች አሁንም ተይዘው እንዳሉ ሲገመት፣ የነፍስ አድን ሰራተኞች የፍለጋ ሥራቸውን አሁንም ቀጥለዋል።
❤8👍3🙏2
September 4, 2026 4.6K 2 1