የአርቲስት ፊሊሞን ገብረህይወት መሰወር እንዳሳሰበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለፀ፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች… — Sheger Press️️ — TG.ME

የአርቲስት ፊሊሞን ገብረህይወት መሰወር እንዳሳሰበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለፀ፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ የ33 አመቱ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ እንዲሁም የፎቶግራፍና ቪዲዮ ባለሙያ አርቲስት ፊሊሞን ከተሰወረ አንድ አመት እንደሆነው አውስቷል፡፡ የጠፋ እለት ቤተሰቦቹ በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ያመለከቱ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የት እንዳለ እንደማይታወቅም አስታውቋል፡፡

በአርቲስቱ መጥፋት ዙሪያ የተጀመሩ ወይንም እየተካሄዱ ስላሉ ምርመራዎች ከመንግስት ባለስልጣናት የተሰማ ነገር እንደሌለም አስረድቷል፡፡ ፊሊሞን በትግራይ ክልል መቀሌ ከሚሰራበት ቦታ ወጥቶ በባጃጅ ወደቤቱ እየሄደ እያለ መጥፋቱ ተገልጿል፡፡ በባጃጅ ከመሳፈሩ በፊት ለባለቤቱ ደውሎ አሳውቋት የነበረ ሲሆን ለረጅም ሰአት ቤቱ ባለመመለሱ መልሳ ስትደውልለት ስልኩን አላነሳም፡፡

ከዚያን እለት ጀምሮ አርቲስቱ የት እንዳለ እንደማይታወቅ የጠቀሰው አምነስቲ ፊሊሞን የሁለት ልጆች አባት መሆኑንም አስታውቋል፡፡ የሚመለከታቸው ባለስልጣናት በአርቲስቱ አፈና ላይ ገለልተኛ፣ ጥልቅና ግልፅ ምርመራ በማካሄድ የት እንዳለና ምን እንደሆነ እንዲያሳውቁ አምነስቲ ጨምሮ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
❤7😱1
September 2, 2026 4.9K 1 2