ለጊዜው ከስራ ታገዱ‼️ 2ቱ የትራፊክ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለጊዜው ከስራ እንዲታገዱ መደረጉ ተገለፀ:: የአዲስ… — Sheger Press️️ — TG.ME

ለጊዜው ከስራ ታገዱ‼️

2ቱ የትራፊክ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለጊዜው ከስራ እንዲታገዱ መደረጉ ተገለፀ::

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ የመንገድ ተጠቃሚዎችን ደህንነት ለማስጠበቅና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለማስፈጸም በሚያከናውናቸው የመስክ ቁጥጥር ስራዎች ወቅት ከመንገድ ተጠቃሚዎች ጋር አለመግባባቶች እንደሚከሰቱ ገልጿል።

በዛሬው ዕለት (ነሀሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም) በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ሲሰራጭ የዋለውን ምስል አስመልክቶ ተቋሙ ባወጣው መረጃ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አብራርቷል፦

• የቁጥጥር ባለሙያዎች ደንብ የተላለፈን አሽከርካሪ የመንጃ ፈቃድ በሚጠይቁበት ወቅት "አልሰጥም" በማለት ስራ ማስተጓጎል፣ ስድብ፣ ዛቻ ወይም ሃይል መጠቀም በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑ ተመልክቷል።

• ተቋሙ በምስሉ ላይ የታየውን አለመግባባት ግራና ቀኝ ያለውን አካል ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በማጣራት ላይ እንደሚገኝና እስከዚያው ድረስ በክስተቱ ላይ የተሳተፉት ሁለቱ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለጊዜው ከስራ እንዲታገዱ ማድረጉን አስታውቋል።

ህብረተሰቡ የችግሩን የማጣራት ሂደት በስክነት እንዲከታተልና ትክክለኛ ካልሆኑ መረጃዎች እንዲቆጠብ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
❤10👎1🤔1
September 2, 2026 2.1K 3 9