በበዓል ሰሞን የሚታየውን ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ… — Sheger Press️️ — TG.ME

በበዓል ሰሞን የሚታየውን ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለፁት የበዓል ገበያን ተገን በማድረግ የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከል በመላው ከተማዋ ጥብቅ የቁጥጥር ስራ መጀመሩን አስታውቋል።

ቢሮው በተለይም የኢንዱስትሪ ምርቶች በሚሸሸጉባቸው መጋዘኖች ላይ ድንገተኛ ፍተሻዎችን እያከናወነ ሲሆን፣ ምርት በመደበቅና ሰው ሰራሽ እጥረት በመፍጠር ዋጋ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

የቁጥጥር ስራው የምርት ጥራትንና ደረጃን ማረጋገጥን የሚያካትት ሲሆን፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ለጤና ጎጂ የሆኑ ምርቶች ለገበያ እንዳይቀርቡ በየደረጃው ያሉ ተቆጣጣሪዎች ስምሪት ተሰጥቷቸዋል።

በተለይም በስጋ ቤቶች፣ በዱቄትና በዳቦ መሸጫዎች ላይ የሚታዩ የምርት መጠን ማነስ ችግሮችን ለመከላከል ክትትል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

ህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ዝውውርን ለመቆጣጠርም ከጸጥታ ግብረ-ኃይሉ ጋር በመቀናጀት በመግቢያ በሮችና በዋና ዋና የንግድ ማዕከላት ላይ ጥበቃና ፍተሻው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተደርጓል።

የቁጥጥር ሰራተኞቹ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ልዩ መለያ (ባጅ) እና ባርኮድ ያለው መታወቂያ እንዲይዙ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም ደንበኞችን ከሐሰተኛ ተቆጣጣሪዎች ለመጠበቅ ይረዳል ተብሏል።

ህብረተሰቡ በገበያ ውስጥ የሚታዩ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎችን፣ የምርት ጥራት ጉድለቶችንና ሌሎች ህገ-ወጥ ተግባራትን ሲመለከት በነጻ ስልክ መስመር 8588 ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
 
❤7👍2😢1
September 2, 2026 4.6K 1 2