የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏 የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር… — Sheger Press️️ — TG.ME

Sheger Press️️Photo
የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር ይታሰባል 

ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡ 

ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡ 

ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል  ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132


የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921
👍9🥰5🙏4❤2
September 2, 2026 4.4K 1