በአውሮፕላን ውስጥ “እውነትን የመስማት ግዴታ አለባቸው” በሚል ስብከት ያቀረበችው ፕሮቴስታንት ወንጌላዊት… — Sheger Press️️ — TG.ME

በአውሮፕላን ውስጥ “እውነትን የመስማት ግዴታ አለባቸው” በሚል ስብከት ያቀረበችው ፕሮቴስታንት ወንጌላዊት  በአየር መንገዱ በረራ እንዳታደርግ ታገደች

ታዋቂዋ አሜሪካዊት ወንጌላዊት እና የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዊትኒ ሊን (Whitney Lynn)፣ በትላንትናው ዕለት ከኦርላንዶ ወደ ሳንዲያጎ በሚጓዝ የአላስካ አየር መንገድ (Alaska Airlines) በረራ ላይ....

የአውሮፕላኑን መተላለፊያ መስመር በመያዝ ስብከት በማቅረቧ እና የበረራ ሰራተኞችን መመሪያ ባለማክበሯ ከአውሮፕላን እንድትወርድ ተደርጋለች።

አየር መንገዱ ለደህንነት አስጊ የሆኑ ባህሪያትን በፍፁም እንደማይታገስ በመግለጽ፣ የ40 ዓመቷን ወንጌላዊት ከአላስካ አየር መንገድ፣ ከሃዋይያን አየር መንገድ እና ከሆራይዘን ኤር በረራዎች ላይ በጊዜያዊነት ማገዱን አስታውቋል።

ወንጌላዊቷ በረራው ከመነሳቱ በፊት በነበረው የሰዓት መዘግየት ወቅት በአውሮፕላኑ መተላለፊያ ላይ በመቆም መስበክ የጀመረች ሲሆን፣ ተጓዦች...

በአውሮፕላን ውስጥ ተዘግቶባቸው ስላሉ “እውነትን ከመስማት ውጪ ሌላ ምርጫ የላቸውም” የሚል እምነት እንዳላት በግልፅ ተናግራለች።

የበረራ ሰራተኞቹ ደጋግመው እንድትቀመጥ እና ንግግሯን እንድታቆም ቢጠይቋትም፣ እርሷ ግን ጥያቄውን ውድቅ በማድረጓ የደህንነት ሰራተኞች ተጠርተው ከአውሮፕላን እንዲያስወጧት ተደርጓል።

ከአውሮፕላን ከተባረረች በኋላ ባስተላለፈችው መልዕክት፣ በአየር መንገዱ የተወሰደውን እርምጃ “መንፈሳዊ ውጊያ” ስትል የጠራችው ሲሆን፣ እራሷንም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስደት ከደረሰባቸው ታላላቅ ሰዎች ጋር አነጻጽራለች።

አላስካ አየር መንገድ በሰጠው መግለጫ፣ ማዕቀቡ የተጣለው የበረራ ሰራተኞችን የስራ ደህንነት ለማስከበር እና የደንበኞችን ምቾት ለመጠበቅ ሲባል መሆኑን አስታውቋል።

ይህ ክስተት በሶሻል ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ክርክር ያስነሳ ሲሆን፣ ብዙዎች “በአውሮፕላን ውስጥ ሰዎችን አስገድዶ ማሰማት የሌሎችን መብት መጣስ ነው” ሲሉ፣ ጥቂቶች ደግሞ “የሃይማኖት ነፃነት ሊከበርላት ይገባል” በሚል እየተከራከሩ ይገኛሉ።

በሀገራችን ኢትዮጵያ መሰል የፕሮቴስታንት አማኞች   በየመንገዱና በየገበያው ማዕከል በብዛት ያከናውናሉ ። እንዲሁ ማድረጋቸው ትክክል ነው ? አይደለም ? በጨዋነት ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ ?

    
❤9👏2
September 1, 2026 3.4K 4 3