አዲስ አበባን በሚመለከት አዲስ ምክረ ሐሳብ መቅረቡ ተነገረ
#Ethiopia:
ከቀረቡት 400 ያህል ምክረ ሐሳቦች በ396ቱ ላይ ያለ ልዩነት መስማማት ተችሏል ተብሏል
የአዲስ አበባ ሕጋዊ ባለቤትነትን ጉዳይ አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ባቀረቡት ቅሬታ፣ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለውሳኔ ሰጪው አካል ለሚያዘጋጀው የተጠቃለለ ምክረ ሐሳብ ዕገዛ ለማድረግ አዲስ የተዋቀረው ኮሚቴ፣ አዲስ አበባ የፌዴራል መንግሥት ‹‹አካል ናት›› የሚለው ቀርቶ ተጠሪ ትሁን የሚል ምክረ ሐሳብ ማቅረቡ ተነገረ።
የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ ከተማ መሆኗ በሕግ ይደንገግ በሚል ያቀረቡትን ቅሬታና የ500 የሥራ ቡድን አዲስ አበባ የፌዴራል መንግሥት ‹‹አካል ናት›› እንዲባል የተስማማበትን ምክረ ሐሳብ የተመለከተው አዲስ የተዋቀረው ኮሚቴ፣ ‹‹የፌዴራል አካል ናት›› መባሉ ቀርቶ ‹‹የፌደራል መንግሥቱ ተጠሪ›› በሚል እንዲተካ ምክረ ሐሳብ ማቅረቡን ተመካካሪዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል።
120 አባላት ያሉት የአጀንዳ አጠናቃሪዎች ቡድን፣ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ለስምንቱ የ500 የሥራ ቡድን ያቀረበው የተጠቃለለ ምክረ ሐሳብ ከተነበበ በኋላ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ባለቤትነት ጉዳይ ከኦሮሚያ ክልል ተወካዮች የቀረበውን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ ለመስጠት የተዋቀረው ኮሚቴ የመጨረሻ ውሳኔ፣ አዲስ አበባ ‹‹የፌዴራል አካል ናት›› የሚለው ተስተካክሎ ‹‹ተጠሪ ትሁን›› በሚል እንዲተካ ኮሚቴው ምክር ሐሳብ ማቅረቡን ለ4,000 ጉባዔተኞች በንባብ መቅረቡን ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
በ500 የሥራ ቡድን መግባባት ላይ የተደረሰባቸውን ምክረ ሐሳቦች ለማቀናጀት የተቋቋ...
1
61
16
2
61
16
2August 31, 2026 4.8K 9 3