የጠንቋዩ ዋሻ🗻 🙈ክፍል 14🙈 💔💔💔🗾💔💔💔 ጠንቋዩ አቢያራ በዋሻው ውስጥ አስተዳድራቸዋለው ብሎ… — yefkr kal😘😘😜😘❤❤❤ — TG.ME

🗻የጠንቋዩ ዋሻ🗻 🙈ክፍል 14🙈 💔💔💔🗾💔💔💔 ጠንቋዩ አቢያራ በዋሻው ውስጥ አስተዳድራቸዋለው ብሎ የሚያስባቸውንና እንደባሪያው የሚያዛቸውን አገልጋዮቹን ዛሬ በተለየ መልኩ ሰብስቧቸዋል ፣ ሁሉም የመሰብሰባቸው ምክንያት ስላልተገለፀላቸው እርስ በእርስ ከመተያየት በቀር ምንም መተንፈስ አልቻሉም አቢያራ ዙፋኔ ብሎ ከሚጠራው ትልቅ መቀመጫላይ ጥቁሩን አስፈሪ አልባሳቱን እንደለበሰ ቀያይ ዛጎሎች በእጁ ይዞ እያወዛወዘ አጎንብሶ በቀስታ የማይገቡ ቃላቶችን እያወጣ ነው ፣የአቢያራ ሴቶች እንዳቀረቀሩ ናቸው ፣ አልፎ አልፎ ኤዛ ብቻ ባልተለመደ ጭንቀት ተወጥራ በጨረፍታ ወደመሳይ አየት የምታደርገው ፣የሆነ ነገር ሸቷታል አቢያራ አንዳች ነገር ለማድረግ እስካላሰበ ድረስ በዚ መልኩ አይሰበስባቸውም ወይ በሷ ላይ ወይ በመሳይ ላይ አንዳች ጉዳት ሊደርስባቸው እንደው ተሰምቷታል ።። ኤሊያታ እንዳቀረቀረች ከፊትለፊቷ ስለምትሰማው የአቢያራ ሹክሹክታ አንድ ነገር ለመረዳት ጥረት እያደረገች ነው ፣ ኤፍራም ግራ እንደገባት ነው ያለችው አድማስ አቢያራ የሚያዘውን ሁሉ ለመፈፀም ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ነው ፣ መሳይ የአቢያራን አንገት የሚቀነጥስበት አንድ ስለት በድንገት እጁላይ እንዲያርፍ ተመኘ አነመስፍን ምን ያጠፋነው ነገር ይኖር ይሆን ብለው በራሳቸው ውስጥ በጨንቀት ጠፍተዋል ። ቤቱ እንዲ በፀጥታ ሲታመስ ቆይቶ ፣ ድንገት አቢያራ ብድግ ብሎ ሲቆም የሁሉም ልብ ቀጥ ያለ መሰለ ።አቢያራ ጥቂት ሲንጎራደድ ቆይቶ በአስፈሪ እና የተሰበረ በሚመስል ድምፅ መናገር ጀመረ " "እእእእ ዛሬ እዚ የሰበሰብኳቹ አባቴ አንድ ነገር እንዳደርግ ስላዘዘኝ ነው እኔን በእናንተ ላይ የሾመኝ አባቴ የኔ ጌታ ከልጆቼ ውስጥ አንዷን መስዋት እንዳደርግ አዞኛል እንደምን እንቢ ማለት ይቻለኛል ፣በርግጥ ልቤ አዝኗል ግን አባቴ የኔንም ሕይወት ቢጠይቀኝ እሰጠዋለው ልጆቼ ለአባታቹ ጥያቄ መቼስ በደስታ መላሾች ናቹ እኔም ልክ እንደዛ ነው ያሳደኳቹ እናም አንድ ነገር ያጎደለች ልጅ አለች ከናንተ መካከል ለዚህም ነው አባቴ ወደሱ የጠራት "ብሎ አቢያራ ፀጥ ሲል መሳይ በጥላቻና በፍራቻ ቀና ብሎ ተመለከተው ፣ይሄ ጠንቋይ ሴጣንነቱ ይበልጥ ጨምሯል ማለት ነው ሰውን እያጭበረበረ የደም ጥማቱን እየተወጣነው ፣በቃ ኤዛን ሊያጠፋት ነው ስለኔና ስለሷ አውቋል ማለት ነው ብሎ በማሰብ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ ። አድማስ ኤዛን ዞር ብሎ አይቶ አቀረቀረ ኤዛ አድማስ ሲያያት ይሄ ድግስ ለሷ እንደሆነ በማሰብ በፍርሃት አድማስ በቀኝ እጁ የያዛትን የተሸፈነች ስለት ተመለከተች ፣ ኤልያታ ለጓደኛዋ በማዘን ዞራ አየቻት እናም በአንድ አይኗ እንባዋ ኮለል አለች እህታማችነታቸው ማብቂያው ደረሰ ልጅነታቸው የዋሻው ውስጥ የፀጥታ ኑሯቸው ታወሳት ግንአቢያራ ካለ አለ ነው በቃ ፣እነ መስፍን ጉዳዩ እነሱን ስለማይመለከት በግልግል መንፈስ ተንፍስ አሉ ፣ እነሱም የአቢያራ ተጠቂ የምትሆነው ኤዛ እንደሆነችና ለዚሁሉ ችግር የዳረጋት ደሞ ጓደኛቸው መሳይ እንደሆነ ተሰምቷቸዋል ። አቢያራ ከጎነ በጣም ቀረብ ብሎ ወደቆመው አድማስ እያየ ይበልጥ እንዲቀርበው ምልክት ሰጠው ። አድማስ ስለቱን እየነካካ ወደ አቢያራ ተጠጋ አቢያራ ለአድማስ በሹክሹክታ ተናገረ በዚ ጊዜ አድማስ ግራ በመጋባትና በድንጋጤ አቢያራ ላይ አፈጠጠ ፣አቢያራ መልህክቱን እንደዘበት ለአድማስ ከነገረ በዋላ ወደ ኤሊያታ አፈጠጠ እናም እረጃጅም ጥፍር አማ ጣቶቹን ወደ ኤልያታ ቀስሮ "የኔ ልጅ አንቺ የጌታዬ ምርጫ ነሽ "ብሎ በሚያስፈራ ድምፁ ኤልያታን እንድትቀርበው ጠራት ። እዛ የነበሩት ሁሉ ግራ በመጋባት አንዴ ኤልያታን አንዴ አቢያራን ተመለከቱ ኤልያታም አልገባትም ነገር ግን ወደሱ መንቀሳቀስ ስትጀምር አድማስ የሚያፈቅራትን ሴት በገዛ እጁ እንዲሰዋት በመታዘዙ ዘገነነውና አይደረግም ብሎ ሳያስበው ጮኽ ፣ በዚ ድምፁ ጠንቋዩ እራሱ ሳይደነግጥ አልቀረም ፣ መሳይ የአድማስን ቁጣ ሲያይ ደስ አለው በዚ አጋጣሚ አንድ ነገር ለመፍጠር እራሱን አዘጋጀ ........ ✍ ሙና መሀመድ ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን @samketn አድርሱኝ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 @samketn @samketn ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️

August 20, 2024 3.1K 4