✍✍የጠንቋዩ ዋሻ✍✍ ★፠፠ክፍል 13፠፠★ ♦♥♦♥♦♥♦♥♦♥♦♥♦ መሳይ የድምፁ አሰቀያሚነት እና የኮሽታው ሁኔታ ልቡን እርብሽ አደረገበት ፡እዛ ዋሻውስጥ ካመጡት ጀመሮ ምንም ሰላም ባይሰማውም ፡በዚ ሁለት ቀን ግን የበለጠ ነገሮች አስፈሪነታቸው ፡እየጨመረበት መጥቷል ፡ በዚጊዜ ደሞ ፡ ጓደኞቹም ተጨማሪ ፍርሃቶቹ ሆነዋል ፡ አስተያየታቸውንም እየወደደው አይደለም ፡ ድምፁ እየቀረበው ሲመጣ የዋሻውን ግድግዳ ተደግፎ ፡በመቆም ፡ ፈጣሪውን መለመን ጀመረ ፡'አምላኬ ሆይ ፡ከመጣው ነገር ሁሉ ከልለህ ከዚጉድ አውጣኝ እስካሁንም በጥበብህ ጠብቀኽኛል አሁንም አንተ ሸፍነኝ እኔ ይሄን ሁሉ የምችልበት አቅም የለኝም እባክህ'ብሎ ተማፀነ ከፍርሃቱ የተነሳ ዕንባው እየወረደ ነበር በቃ ዛሬ ሊያልቅልኝ ነው መሰለኝ እነዚ እብዶች ጉድ ሊያደርጉኝ ነው እዚ ጨለማ ዋሻ ውስጥ ,,,,,,,,,,,,,, የሚያስፈራራው ድምፅ አጠገቡ ሲደርስ ቀመ፡ የሱም ልብ ቀጥ አለ ለአፍታ " የጨለማው ጌታ የዓለም ሁሉ አይል በጄ ይረፍፍፍፍፍ ሁሉንም የሚቆጣጠር አይል ስጠኝኝኝኝኝኝ ማንም ከቃሌ አይውጣጣጣጣ የጨለማው ሰላም ይጠበቅቅቅቅቅ ፈረሶቼን በአረቱም አቅጣጫ እንድጋልባቸው አይሉን በኔላይ አውርድድድድ አይሉ የኔ ይሁንንን ጨለማው ይንገስስስስስ ብርታቱ ሁሉ በኔላይ ይደርርርርር አሆሆሆይ አቢያራራራ,,,,,,,,,' የሚያስጨንቅ እና የሚያስፈራራው የአቢያራ ድምፅ ነበረ መሳይ ጭንቀቱ የበለጠጨምሮ እግሩ ተብረከረከበት ፡ ከአሁን አሁን ያዘኝ ብሎ በጣም ፈራ ፡ ነገርግን አቢያራ ጥቂት መሳይ ባለበት ቦታ ከቆመ በዋላ ያንን የጥንቆላ ጩኽቱን እያሰማ በዋሻው ውስጥ ያለምንም ብርሃን እየተዟዟራ ቀጠለ ፡መሳይ አልፎት ሲሄድ አላመነም ፡ እንደምንም ብሎ የሚንቀጠቀጥ እግሩን እየጎተተ ወደ ማደሪያው ሄደ ፡የሚያድርባ ትንሽዬ የዋሻው ክፍል ጋር ሲደርስ በግልግል ተነፈሰ ፡ ወደውስጥ ፡በመግባት ፡መኝታው ላይ ተዘረጋ ፡መልሶ በመነሳት መዝጊያውን በጥንቃቄ ዘጋውና እዛው መዝጋውን ተደግፎ ቆመ፡ እናም አይኑን ጨፍኖ ፡ እስከመቼ በዚ መልኩ እንደተሳቀቀ እንደሚኖር ፡እራሱን ጠየቀ ፡ እንዴት ነው ፡ከዚ ጉድ ማምለጥ የሚችለው በሆነ ዘዴ ከሁሉም ጋር መጋፈጥ አለበት በቃ፡ መሞቴ ካልቀረ ሞክሬ ብሞት አይሸለም ፡ አዎ ይሄንን የጭካኔና ያለማወቅ ሰንሰለት መበጣጠስና ማምለጥ አለብኝ !!! አይኑን ገለፀና የዋሻው ግድግዳላይ አሳረፈ አንዳች ብርሃን ያየ መሰለው ፡ተንበርክኮ ለፈጣሪው ከልቡ ፀሎቱን አደረሰ ፡ ከዚ በዋላ ለሚያደርገው ነገር ሁሉ ይቅርታንም ጠየቀ ፡ እናም አልጋውላይ ተንጋሎ ፡እቅድ ማውጣት ጀመረ ፡ ይሄንን የሴጣን ጎሬ መበታተን እና ነፃ መውጣት ፡ያለበት በራሱ ጥንካሬ ነው ፍርሃትና መረበሽ መጨረሻው ሞት ነው ፡ ስለዚ እነዚህን ሰዎች አንድ በአንድ ለመጋፈጥ ወሰነ ,,,,,,,, ♦♦♦♦♠♠♦♣♣♣♣ ¥አድማስ በጠዋት መጥቶ የተዘጋውን የመሳይን በር ሲያንኳኳ መሳይ በድንጋጤ ተነስቶ ቆመ "ማነው እእ" "እኔነኝ አንተጩጬ ክፈት በሩን "አለው ቆጣ ብሎ "ለምን"አለ መሳይ እንደዛ ምስኪን ሰውዬ ሊያርዱኝ ነው እንዴ ሊቀድሙኝ እንዳይሆን "ክፈት እንጂ ለምን ይላል እንዴ!"አለ ቁጣው ሰይበርድ "ባልከፍትስ "አለ መሳይ ፍርሃቱ ሳይለቀው ፡እናም በዙሪያው አንዳች ስለት ነገር እየፈለገ ፡ነገር ግን ያለሰአን ምንም የለም "አንተ የማትረባ ፈልፈላ ጌታ አቢያራ ቢፈቅድልኝ ፡አንድ ቀን አላሳድርህም ነበር አንገትህን አንቄ ለዘንዶ ነበር የምሰጥህ "አለው በጩኽት ፡ ይሄን ጩኽት ሰምታይሆን አይታወቅም ፡ ኤልያታ የተባለችው ፡ የአቢያራ ሴት ፡ድምጿን አሰማች "አድማስ ምንድነው "ስትል፡አድማስ ተርበተበተ ኤልያታን በጣም ስለሚወዳት ፡ የሷን ድምፅ ሲሰማ የሌለ ይለሰልሳል "አይ ሰላም ነው መሳይ አልወጣም ሲለኝ ተናድጄ ነው" "መሳይ መተኛት ከፈለገ ተወው ለምን ፈለከው" "አይ ለሱ አንድ ማስጠንቀቂያ ነበረኝ ለዛ ነው"አለ አድማስ ፡መሳይ ማስጠንቀቂያ አለኝ ብሎ ለኤልያታ ሲነግራት ፡ተጨነቀ በቃ ትላንት ከኤዛ ጋር አይቶኛል ብሎ "እሺ ማስጠንቀቂያውን በዋላ ሲነሳ ትነግረዋለህ እንቅልፉን ይጨርስ ይደርሳል ፡"አለች በትህዛዝ አይነት ፡ "እሺ ካልሽ ፡ግን እኔ ወደከተማ ልወጣ ነው የጀኔተሮቹ ነዳጅ ስላለቀ ማምጣት አለብኝ"አለ ቅር እያለው "ከሆነ ማስጠንቀቂያህን ልትነግረኝ ትችላለህ እኔ አናግረዋለው "አለች ኤልያታ ፡ መሳይ የአቢያራ ሴቶች እረጅም ወሬ ሲያወሩ ሰምቶ አያውቅም ኤዛም ትንሽ ስለቀረበችው እንጂ ፡የኤልያታ የሚያምርና የሚስረቀረቅ አይነት ድምፅ እየገረመው ፡የማስጠንቀቂያው ጉዳይ እያሳሰበው ፡ ጆሮውን ጣል አድርጎ ሰማቸው "እእሺ ግን ላንቺ ,,,,," "ለማንም ተናገርከው ለውጥ አየመጣም ተራ ነገር ከሆነ አትንገረኝ ወደስራህ መሄድ ትችላለህ "አለችው ፡ አድማስ በሚያፈቅራት ሴት እንደተራ መታየት ስላልፈለገ"ኤልያታ ምን መሰለሽ ፡መሳይ እእእ ማለቴ ኤዛን እያታለላት ነው ፡ ማለቴ ወደሱ እንድትሳብ ፡በማድረግ ችግር ውስጥ እየከተታት ነው ፡ እና ይሄን ደሞ ጌታዬ ከሰማ ታውቂያለሽ ፡ከዚ በፊት እንደተፈጠረው ያልጅ ፡በኤዛ ምክንያት የተገደለው፡እንደዛ ነው የሚፈጠረው"ብሎ ዝም አለ "እና አንተን ምን አሳሰበህ እና ነው ማስጠንቀቂያ የምትሰጠው ፡ አባታችን ያውቅ ይሆናል ፡ደሞ ከሱ ምንም አይሸሸግም ብታስጠነቅቀውም አባታችን ቀድሞ ፡አውቆት ይሆናል ዝም ያለው ፡ ነው ይሄንን ልጅ መርዳት ፈልገሃል "ብላ አፋጠጠችው "ኧረ እኔ እንደዛ አላሰብኩም "አለ ጭንቅ እያለው "በቃ ወደ ምትሄድበት ሂድ "ብላው እስኪሄድ ጠብቃ እሷም መሳይን ምንም ሳትለው ሄደች ፡መሳይ በግልግል ተነፈሰ ፡ በቃ ከኤዛ ጋር ያለው ነገር ሁሉንም የሚያሳስብ ከሆነ ጉድ ነው የሚፈላው ምክንያቱም ኤዛ እንደወደደችው ገብቶታል ፡ ምን አልባትም ፡እሱን አንድ ነገር እንዲያደርጉት አትፈቅድ ይሆናል ፡ ወይም ደሞ ፡እራሷንም ፡ይገሏት ፡ይሆናል ፡ እንግዲ የሁለቱን ግንኙነት አድማስና ኤልያታ ሰምተዋል ፡በቀጣይ ፡ደሞ ፡ሌሎቹ ጋር መድረሱ አይቀርም ይሄ ከመሆኑ በፊት እና ሁለቱም ፡ከሚ ጠፉ ቀድሞ አቢያራ የተባለውን ፡ሴጣን፡እሱ እራሱ ቀርቦ ማጥፋት እንዳለበት አመነ ግን እንዴት ?,,,,,,,,,, ✍ ሙና መሀመድ ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን አድርሱኝ @samkatn ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 @samkatn @samkatn ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
የጠንቋዩ ዋሻ✍✍ ★፠፠ክፍል 13፠፠★ ♦♥♦♥♦♥♦♥♦♥♦♥♦ መሳይ የድምፁ አሰቀያሚነት እና የኮሽታው ሁኔታ… — yefkr kal😘😘😜😘❤❤❤ — TG.ME
August 20, 2024 2.2K 1