የጠንቋዩ ዋሻ✍✍ ♦♦♣ክፍል 12♣♦♦ °❖°❖°❖°❖°❖°❖° መሳይ በኤዛ ቀጭን ወገብ ላይ እጆቹን ጠምጥሞ… — yefkr kal😘😘😜😘❤❤❤ — TG.ME

✍✍የጠንቋዩ ዋሻ✍✍ ♦♦♣ክፍል 12♣♦♦ °❖°❖°❖°❖°❖°❖° መሳይ በኤዛ ቀጭን ወገብ ላይ እጆቹን ጠምጥሞ ወደራሱ እያስጠጋ ቀልቧን ይገዛው ጀመረ ፡ ኤዛ የስሜት ቁንጥጫውን ተቆጣጥራ ማስቆም እስኪሳናት ሆና በዝምታ ተከተለችው ፡ የልቧ ምት ለራሷም እስኪገርማት ሆነች ፡ መሳይ በአሳዛኝ አይኖቹ አይኖቿን ፈልጎ አተኮረባቸው ፡ ኤዛ አይኖቹን ተከትላ ወደ ከንፈሮቹ ዝቅ አለች ፡መሳይ ያቀረበችለትን እነዛን እንጆሪ የመሱሉ ከንፈሮቿን በፍጥነት ተቀበላቸው ፡ እሱ እንደተራበ ሰው ሲሆንባት እሷ በማታውቀው አዲስ ስሜት ተቀጣጠለች ፡ ይሄ ለሷ ለየት ያለ ሌላ አዲስ የሕይወት መንገድ ነው ፡ ተስሞ የማያውቀው ከንፈሯ ፡ግን ቦታውን አልሳተም ፡ እሱ የሚያደርገውን እየተከተለች ፡ በመሳይ ከንፈሮች ላይ ፈሰሰች ፡ መሳይ ጠበቅ እያደረገ ልቧን አጠፋው ፡ ፡ እንዲ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጠፍተው ሲወዛወዙ ፡ከወደዋሻው ደውል ተሰማ ፡ኤዛ ብርግግ ብላ መሳይን ገፍትራው ድንብርብር ብላ ቆመች ፡ መሳይ በድንጋጤ ቀጥሎ የምታደርገውን ጠበቀ፡ ትንሽ ስታየው ፡ቆይታ "ና ቶሎ እንግባ ፡አባት አቢያራ ነው የደወለው ፡ እኔ እንዳልገባው አውቋል ፡ ይቅር ይበለኝ አባቴ "አለች እየተርበተበተችና የመሳይን አጅ እየያዘች ፡ "እኔ ለብቻዬ ልሂዳ ፡አብረን ካየን ሊቆጣ ይችላል"አላት እጁን አይዛ ወደዋሻው እየጎተተች ስትወስደው "አይቶናል ፡ቀጣይ የምቀጣውን ቅጣት መቀበል ብቻ ነው "አለች ትንፋሿ ቁርጥቁርጥ እያለ "ኧረ አላየንም እዚ ማንም አልነበረም እኮ"አለ መሳይ "አይ አይ አቢያራ በልባችን ውስጥ አለ ጌታዬ "አለች በቁጭት "እንዲማ መቼም ሊሆን አይችልም በልባችን የሚኖረው ፈጣሪ ብቻ ነው ፡ ፈጣሪ ደሞ ብርሃን ነው ፡ እንደ አቢያራሽ ጨለምተኛ እና ሰውም አይደለም ......."ብሎ ሊቀጥል ሲል "ዝም በል አንተ ልጅ ችግር ውስጥ አትክተተኝ ፡አፍህን ዘግተህ ወደውስጥ ግባ ነገ እንገናኛለን በ"ብላው ፡በስተግራ ካለው የዋሻው ጨለማ ክፍል ውስጥ ገብታ ተሰወረች ፡ መሳይ ቀስ እያለ ወደማደሪያው ለመግባት የዋሻውን ግድግዳ እየታከከ በጨለማው ተጓዘ ፡ የዋሻው ውስጥ ነብሳቶች ሲርርርር ማለት ጀምረዋል ፡ የተለያየ ደምፅ ሲሰማ ልቡ መምታቱን ዛሬም አላቆመም፡ ሊለምደውም አልቻለ ፡ በፍርሃት ፡ እንደተወጠረ ፡ ግድግዳውን እየታከከ ሲሄድ ፡ ለየት ያለ ድምፅ የሰማ መሰለውና ወደዋላው ለመመለስ ቃጣው ፡ እናም ባለበት ቆመ ፡ ድምፁ ደሞ እየቀረበው መጣ ፍርሃቱ ጨመረ ኦርርርር ኡኡኡኡኡ ስስስስስስ ሽሽሽሽሽሽሽ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ✍ ሙና መሀመድ ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን @samkatn አድርሱኝ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 @samkatn @samkatn ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️

August 20, 2024 1.8K 3